16ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ምክኒያት በማድረግ ሚዲያ ጉብኝት ተደረገ፣

    16ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል በፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነት በድሬዳዋ አስተዳደር አስተናጋጅነት “ወንድማማችነት ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሃሳብ እየተከበረ ነው ።
    የበዓሉ አንዱ አካል የሆነው የአስተናጋጇ የድሬዳዋ አስተዳደር ታሪካዊ ስፈራና የልማታዊ እንቅስቃሴዎች በሚዲያ ባለሙያዎች ጉብኝት ተደረጓል።
    በጉብኝቱም መርሃግብር በፋሽስቱ ጣልያን ወረራ ጌዜ ከአርበኞች ጋር በመሰለፍ የተሰውትን የአፍሪካዊያን ወንድሞቻችን መካነ መቃብር ጉብኝተዋል። ዓላማውም አፍሪካውያን ለነጻነታቸው በጋራ የመፋለም ታሪክ ያለና አሁንም የምዕራባውያን በእርዳታ፣በዲሞክራሲና በሰብዓዊ መብቶች ሽፋን ዘመናዊ የእጃ ዙር የቀኝ አገዛዝ ጫና ለመላቀቅ የጋራ ታሪኩ መነቃቃት እንደሚፈጥር ከጉብኝቱ መገንዘብ ይቻላል ።
    ጥንታዊና ታሪካዊ የኢትዮ- ጂቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አግልግሎት ያለበት ሁኔታ በሚዲያ ባለሙያዎች የተጎበኘ ሲሆን የኢትዮ ጂቡቲ ምድር ባቡር ከከተማዋ አመሰራራት ጋር ያለው ቁርኝት እና አሁን ያለበት ሁኔታን የተመለከተ ሰፊ ማብራሪያ በድርጅቱ ስራ አስኪያጅና ባለሙያዎች ተደርጎላቸዋል።
    የድሬዳዋ ሙዝየም ፣ ሚሊኒየም ፓርክ ሽሙ ሳሙና ፋብሪካ፣የአፍሪካዊያን መካነ መቃብር ከተጎበኙ ቦታዎች ይጠቀሳሉ።
    የዋልታ፣ፋና፣ኢቲቪ፣ኦቢኤን፣አማኮ፣ጋንቤላ ቲቪ፣ደቡብ ቲቪ፣ድሬ ቲቪ ኢዚኣ የመንግስትኮ.ጉ.ቢሮ የሚዲያ ባለሙያዎች የጉብኝቱ ተሳታፊዎ ናቸው።