የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን ለ16ኛ ጊዜ #ወንድማማችነት ለህብረብሄራዊ አንድነት$ በሚል መሪ ቃል በድሬዳዋ አስተናጋጅነት ለሚከበረው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን ለመላው ኢትዮጵያዊያን የእንኳን አደረሳቹ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ክብርት አፈ-ጉባኤዋ በመልእክታቸውም ዘንድሮ ለ16ኛ ጊዜ በውቢቷና የኢትዮጵ ብሄር ብሄረሰቦች በወንድማማችነትና በፍቅር በሚኖሩባት ትንሿ ኢትዮጵያ ድሬዳዋ መከበሩ ልዩ የሚደርገው ለዘመናት የኢትጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ሲጠይቁ የነበረው ነጻ ፣ ገለልተኛና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ተካሂዶ አዲስ መንግስት በተመሰረተበት ማግስት እና በኢትዮጵያን ህልውና ላይ የተቃጣውን የውስጥና የውጪ ጥቃት ለመመከትና ታሪካዊውን አድዋን ለመድገም መላ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ከባንዳዎች ጋር ጦርነት ላይ በሚገኙበት ወቅት በአሉ በድሬዳዋ መከበሩ እንደ ልዩ እድል እንደሚቆጠር ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም አሉ ክብርት አፈ-ጉባኤዋ ሁሉም የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ከአሁን በፊት በብሄር ብሄረሰቦች ስም ሲገነባ የነበረውን የጥላቻ ግንብ አፍርሰው በወንድማማችነትና አንድነት የኢትዮጵያን ሉአላዊነት፣ ነጻነትና ብልጽግናን ለማስቀጠል ቃል ወደምንገባበት እና እውነተኛ ህብረብሄራዊ ወንድማማችነት ወደሚገለጽበት የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በአል የሚመጡ ብሄር ብሄረሰቦችን ለመቀበል ድሬዳዋ ዝግጅቷን አጠናቃ እንግዶቿን በመጠባበቅ ላይ መሆኗን በመግለጽ የድሬዳዋ አስተዳደር ማህበረሰብም የሚመጡ እንግዶችን በድሬዳዋዊ የፍቅር መስተንግዶ በመቀበል የሚታወቁበትን ወንድማዊነታቸውን እንዲያሳዩ ጥሪያቸውን በማስተላለፍ ለመላው ኢትዮጵያዊያን የእንኳን አደረሳቹ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ወንድማማችነት ለህብረብሄራዊ አንድነት !!
ምንጭ፦ድሬደዋ ምክር ቤት


