የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የልማት ተነሺዋች ካሳ ክፍያ መልሶ ማቋቋም ቅሬታ አፈታት ዳይሬክቶሬት ለአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ለህዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት ካሳ የሚከፈልበትና ተነሺዋች መልሰው የሚቋቋሙበት ሁኔታ ለመወሰን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በወጣው አዋጅ ቁጥር 1161/2011 አዋጁን ለማስፈፀም ስልጠና እየተሰጠ ነው።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባወጣው ደንብ ላይ ለአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እየተሰጠ ያለውን ስልጠና የአስተዳደሩ ከንቲባ የተከበሩ ከድር ጆሀር በንግግር ከፍተዋል።


