ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ ወደ ከተማችን ድሬዳዋ የመጡ ዳያስፖራ ማህበረሰብ በድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ በመገኘት ጉብኝት አደረጉ።
ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያ ወደ ሀገር ቤት እንዲገቡ በተደረገው ጥሪ መሰረት የድሬዳዋ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አስተዳደሩ ባዘጋጀው ፕሮግራም ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ። በፕሮግራሙ መሰረት በድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወደ ውጭ መላክ የጀመሩ ፋብሪካዎችን የስራ እንቅስቃሴ የጎበኙ ሲሆን ለዳያስፓራ ማህበረሰብ በሚፈልጉበት ዘርፍ እንዲሰማሩና የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የፓርኩ ስራ አስኪያጅ አቶ ካሚል ኢብራሂም ጥሪ አቅርበዋል።


