በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የጥምቀት በአል ከነገ ጀምሮ ባሉት ቀጣይ ቀናት በድሬዳዋ አስተዳደር በታላቅ ድምቀት የሚከበር ሲሆን ከዚሁ በአል ጋር ተያይዞ የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ እስቂያስ ታፈሰ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰተዋል ።
በአለም ቅርስነት የተመዘገበው የጥምቀት በአል ሲከበር የወንድማማችነትና የአብሮነት እሴቶቻችን ባጎላና ለአለም ህዝብ የጀመርነውን ኢትዮጲያዊ አንድነት ጎልቶ የሚታይበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በአሉ በዚህ አመት ሲከበር ኢትዮጲያዊያንና ትውልደ ኢትዮጲያዊያን ሀገራቸው ገብተው በአሉን በጋራ ከቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ከወገኖቻቸው ጋር ለማክበር ትልቅ እድል መፍጠሩን የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ እስቂያስ ታፈሰ ተናግረዋል ።
በአሉ በዋናነት ሲከበር ሀገራችን በአስቸካይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ እንደመሆኗ መጠን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ እዝ ለበአላት ከሚሰጠው ትኩረት ባሻገር በተለይም የጥምቀት በአል የአደባባይ ሀይማኖታዊ በአል እንደመሆኑ መጠን ለበአሉም በቂ ዝግጅት በማድረግና በአሉ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ አግባብ እንዲጠናቀቅ የሚያስችሉ በቂ ዝግጅቶች በማድረግና በበአሉ ወቅት ሰላማዊ የማይሆን ሁኔታ ሊፈጥሩ የሚችሉ እንቅስቃሴዎችና ስጋቶችን በመለየት በቂ ምላሽ መስጠት በሚችል መልኩ የአስተዳደሩ ፖሊስ ኮሚሽን ፣ አጋዥ የፀጥታ አካላት በጋራ በማቀናጀትና የጋራ እቅድ በማዘጋጀት ወደ ስራ መገባቱንም ነው አቶ እስቂያስ ታፈሰ የተናገሩት ።
አቶ እስቂያስ ታፈሰ አክለውም በአሉ የጋራ በአል ከመሆኑ በዘለለ የእሴቶቻችን መገለጫ የአብሮነታችን ማሳያ በመሆኑ እንደወትሮው ሁሉ ከተማችን ድሬዳዋ ላይ የተጀመረው ሰላም ዘላቂ ለማድረግ ማሳያ የሚሆን በአል ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በአሉ ሰላማዊ በሆነ አግባብ ይከበር ዘንድ የሁሉም ባለድርሻ አካላት አስተዋፆ ስለሚኖረው ከቤተ-ክርስቲያን አባቶችና አስተዳዳሪዎች ጋር በበአሉ አከባበር ዙሪያ ውይይት መካሄዱንም አቶ እስቂያስ ተናግሯል ።
የተለያዩ ሀይሎች በአሉ ሰላማዊ እንዳይሆን የተለያዩ ሴራዎችን በማድረግ በአሉን እንዳያደፈርሱት የእምነቱ ተከታዮች እነዚህን ሀይሎች በንቃት በመከታተልና ከፀጥታ ሀይሎች ጋር በጋራ በመስራት በአሉ በሰላም ይከበር ዘንድ የራሳቸውን ጉልህ አስተዋፆ መወጣት እንደሚገባ አቶ እስቂያስ ተናግረዋል ።
በተለይም በአሉ ሲከበር ከሰንደቅ አላማ ጋር ተያይዞ የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሲኖዶስ ያፀደቀውን የቤተክርስቲያኗ መገለጫ የሆነውን አርማ በትክክለኛው ቦታ ላይ ማለትም በአብያተ-ክርስቲያናትና እምነቱ በሚካሄድበት ቦታ ላይ ብቻ በመስቀልና በመያዝ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባና ከዛ ውጪ ያሉ ሌሎች ሁኔታዎችን በሀይማኖታዊ በአሉ ላይ ይዞ መገኘት እንደማይቻልና ከመፅሀፍ ቁዳሳዊ መልእክቶች ውጪ ሌሎች ላላስፈላጊ ግጭቶች ሊያመሩ የሚችሉ መልእክቶች ይዞ በበእሉ ላይ መገኘት እንደማይቻልም ነው አቶ እስቂያስ ታፈሰ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ያስታወቀው ።


