ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ፣ የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊት አባላት የጥምቀት በዓል የሚከበርበትን ስፍራ የፅዳትና የማስዋብ ስራ አከናውነዋል።
የድሬደዋ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰብሳቢና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የድሬዳዋ አገረ ስብከት የካህናት አስተዳደር ሃላፊ ሊቀ ብርሃናት ቀለመወርቅ ቢምረው ተግባሩ ወንድማማቻዊ አንድንትን በማጎልበት አብሮነትን በማጉላት የሃይማኖት መቻቻልን የሚያጠናክር ነው ብለዋል። ምእመኑ ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን በአሉን በፍፁም ሰላማዊ መንገድ እንዲከበር ማድረግ ይገባዋል ሲሉ ሊቀብርሃናት ቀለመወርቅ ቢምረው መልእክት አስተላልፈዋል። በሌላ በኩል የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ…


