የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የከተማ ኮንስትራክሽን እና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአስተዳደሩ የተለያዩ ተቋማት የስራ አፈፃፀምን ምልከታ አድርጓል፡፡

    የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የከተማ ኮንስትራክሽን እና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመሬት ልማት እና ማኔጅመንት ቢሮ፣ የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ገምግሟል፡፡
    ቋሚ ኮሚቴ የመሬት ልማት እና ማኔጅመንት ቢሮ ቆይታው የቢሮው የ3 ወርና የ60 ቀናት ያከናወናቸው ተግባራት የገመገመ ሲሆን ቢሮው ያለው አፈፃፀም አበረታች መሆኑን በመግለፅ ፡፡በቀጣይ ተቋሙ ካርታ ያላገኙ ዜጎችን በሚመለከት ከቀበሌዎች ጋር አብሮ በመስራት በአጭር ጊዜ ውስጥ የቀሩ ስራዎች እንዲከናወኑ የስራ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
    ቋሚ ኮሚቴ በውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ባደረገው ግምገማም የልማት ተነሺዎች ቤት መሰጠት፣ የጋራ ሽንት ቤት መገንባት፣ ጉድጓድ ቁፋሮዎች እንዲሁም የቧንቧ መስመር ግንባታ መሰራት አስመልክቶ ግምገማ አካሄዷል፡፡
    ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በጉድጓድ ቁፋሮው ላይም በኢንዱስትሪ መስፋፋት ምክንያት መስተጓጎሎችና የቁፋሮ ቦታ ችግር እየሆነበት እንደሚገኝ ለቋሚ ኮሚቴው አሳውቋል፡፡ ቋሚ ኮሚቴው የተነሣውን ችግር ተመልክቶ ውሃ አቅርቦትና የውሃ ጥራት ላይ በተመለከተ መስሪያ ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
    በቀጣይ ቀናት እንደሚቀጥል ከቋሚ ኮሚቴው በተገኘው መረጃ ታውቋል፡፡