#ጥንቃቄ ከድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ለግብር ከፋዮቻችን በሙሉ የተሰጠ ማሳሰቢያ፦

    ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳንድ ማንነታቸው ለጊዜው ያልታወቁ ግለሰቦች በተለያየ የሞባይል ስልክ መስመሮች በመደወል ጥቂት የማይባሉ ግብር ከፋዩቻችን ስልክና የንግድ ድርጅቱን መረጃዎች በማጥናት ከባለስልጣኑ ቢሮ ስልክ የተደወለ በማስመሰል ወደ ግብር ከፋያችን በተደጋጋሚ እየደወሉ ድርጅታቸው ያለ ደረሰኝ ሽያጭ ሲያከናውን የያዙት መሆኑን እና በሌላ ህገ-ወጥ ተግባር ውስጥ እንደተገኘ መረጃ ያላቸው መሆኑን በመግለፅ ጉዳዩ በህግ የሚያስጠይቅ እና የሚያሳስር ስለሆነ ወደ ህግ ከማስተላለፋችን በፊት እንደራደር በማለት በተለያዩ ባንኮች በግላቸው የከፈቱትን አካውንት ቁጥር በመስጠት ብር እንዲያስገቡላቸው በማስፈራራት ገንዘብ እየተቀበሉ በባለስልጣኑ ስም እየነገዱ መሆኑን መረጃዎች በተደጋጋሚ እየደረሱን በመሆኑ ጉዳዩ በሚመለከተው የፍትህ አካል ምርመራ እየተደረገበት ስለሆነ ሁሉም ግብር ከፋዩቻችን ይህን ህገ-ወጥ ድርጊት በመረዳት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደርጉ እና ተባባሪ ባለመሆን ተመሳሳይ ሁኔታዎች በሚያጋጥሟችሁ ጊዜ ለባለስልጣኑ እንድታሳዉቁ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡