ቋሚ ኮሚቴው 358 ተጠናቀው ለህብረተሰቡ መተላለፍ ያለባቸውን ቤቶች ገምግሟል፡፡ በተጨማሪም 558 እየተገነቡ ነው፡፡ የተሰሩት ስራዎች የሚበረታቱ እንደሆኑ ቋሚ ኮሚቴው ከገመገመ በኋላ ተጠናቀው ለህብረተሰቡ መተላለፍ ያለባቸውን ቤቶች በፍጥነት ተጠናቀው እንዲተላለፉ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
እንዲሁም በሂደት ላይ ያሉት የጋራ መኖሪያ ቤቶች እና የተለያዩ መሰረተ ልማት ዝርጋታ የሚያስፈልጋቸውን እንዲጠናቀቁ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ በነባር መኖሪያ ቤቶች ፍሳሾች በየመንገዱ ላይ የሚፈሱትንም ቶሎ እልባት እንዲያገኙ ቋሚ ኮሚቴው አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
በተያያዘም በከተማ ልማት ስር የሚገኘው የህብረተሰብ ተሳትፎ የተሰሩ የሰፈር የውስጥ ለውስጥ የኮብል እስቶን ዝርጋታ ፣የጋራ መጸዳጃ ቤቶች፣ የመወጣጫ ደረጃ እና አነስተኛ መሸጋገሪያ ድልድል ገምግሟል፡፡
ይህም ጥሩ እና የሚበረታታ እንዲሁም የህብረተሰቡን ችግር የሚፈታ እንደሆነ ቋሚ ኮሚቴው በመጠቆም ነገር ግን በሂደት ያልተጠናቀቀው እንደ ጋራ መፀዳጃነት ያሉት ተጠናቀው ለህብረተሰቡ መጠቀሚያነት እንዲውሉ በፍጥነት ወደ ስራ እንዲገባም ቋሚ ኮሚቴው አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡


