የህክምና ቁሳቁስ ወደ አፋር ክልል በአስተዳደሩ ከንቲባ ሽኝት ተደረገ ፡፡ በጦርነቱ የወደሙ ሶስት የጤና ጣቢያዎችን መሰረታዊ አገልግሎት ለማስጀመር የተዋቀረው የጤና ቡድን ወደ አፋር ክልል የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ በድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጆሀር ሽኝት ተደረገ ፡፡

    በሽኝቱ መልዕከት ያስተላለፉት ከንቲባ ከዲር ጁሀር ጦርነት ከተከፈተብን ጀምሮ ለሶስተኛ ጊዜ የድሬዳዋ ልዑክ ወደ አፋር እየተጓዘ እነደሆነ አስታውሰው በአሁኑ ጉዞ ሶስት የጤና ጣቢያዎችን መሰረታዊ አገልግሎት የማስጀመር ዓላማን ያነገበ ነው ብለዋል ፡፡
    ለዚህም አገልግሎት ከአስተዳደሩ ሁለት መቶ ሺህ ብር በማውጣት በአጠቃላይ ሶስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር የሚገመት የህክምና ቁሳቁስና ገንዘብ መሳበሰቡን ያሳወቁት ከንቲባው ወደ ሰመራ የሚሄደውን ሉዑክ መልካም ጉዞ እንዲሆንለት ተመኝተው ሸኝተዋል ፡፡
    የጤና ቢሮ ኃላፊ ሲስተር ለምለም በበኩላቸው የህክምና ቁሳቁሱን ያሳባሰቡትን 15 የጤና ተቋማትና ከሁለት የመንግስት ሆስፖታሎች እንዲሁም ከግል ድሬ እና ቤተል መካከለኛ ክሊኒክ የጤና ተቋማትን አመስግነው። የተሰበሰበው ቁሳቁስና ገንዘብ ሶስት ጤና ጣቢያዎችን መሰረታዊ አገልግሎት ማስጀመር የሚችል ነው ብለዋል።