የትራንስፖርት አና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ከክልል ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር የዘርፉን የ2014 በጀት ዓመት አፈፃፀም ገመገመ::
ቢሾፍቱ ሐምሌ 28 ቀን 2014 ዓ.ም፡ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር እና የክልል ትራንስፖርት ቢሮዎች የ2014 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻፀም የክልል ትራንስፖርት ቢሮና የተጠሪ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች፣የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሰረተ ልማትና የትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት እንዲሁም ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የተገኙ ተወካዮች በተገኙበት ተገምግሟል፡፡ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ሰአዳ…


