መድረኩ የክልሎችና አዲስ አበባ መስተዳድር የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ዓመታዊ ሪፖርት እንዲሁም የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ሪፖርት ሰፊ ውይይት የተደረገበትና ተሞክሮና ልምድ የተለዋወጡበት መድረክ እንደነበር ክቡር አቶ ካሊድ አልዋን የብልፅግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል፣በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ገልጸዋል። በድሬዳዋ የመጣው ለውጥ የሚደነቅ መሆኑን የተናገሩት ኃላፊዉ የተገኘውን ስኬት ማስጠበቅና በዘላቂነት ለማስቀጠል ያለንን ወራቶች ካፒታላይዝ በማድረግ በፉክክርና ትብብር ህብረብሄራዊነትን በማጠናከር ግባችንን ማሳካት አለብን ብለዋል።
የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የፓርቲዉ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በበኩላቸዉ እንደ ብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ከፓርቲ ውህደት በፊት የነበሩ ክፍተቶችና ከውህደት በኋላ በአስተዳደሩ በፓርቲና መንግስታዊ ተልዕኮዎች፣ በፀጥታና ደህንነት እንዲሁም በድሬዳዋ መሰረታዊ እሴቶች ዙሪያ የታዩ አጠቃላይ ስኬቶች በዝርዝር ቀርበዉ ግንዛቤ የተወሰደበት መሆኑን ያብራሩ ሲሆን አክለዉም በድሬዳዋ አደረጃጀቶች ህብረብሄራዊ መሰረቱን የጠበቀና ብዝሀ ልሳን ሆኖ ፓርቲው እንዲጠናከር ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።
በመጨረሻም የአሰተዳደሩ ከንቲባ እና የ ፓርቲዉ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ክቡር አቶ ከድር ጁሃር በተገኙበት በፓርቲዉ የ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ምድረ ጊቢ የችግኝ ተከላና የመስክ ምልከታ በማድረግ ሀገራዊ የአደረጃጀት ዘርፍ የ2014 የስራ አፈጻጸም ማጠቃለያና የ2015 መነሻ እቅድ ኦሪየንቴሽ ሀገራዊ የውይይት መድረክ ተጠቃሏል ።


