የድሬዳዋ ደወሌ ምድር ባቡር ድርጅት ለሰራተኞቹ የደሞዝ ጭማሬ ማድረጉን አሰታወቀ።

    የበርካታ ስልጣኔዎች መተግበሪያ የሆነችው ቀዳሚውን ባቡር ወደ ማሀል ከተማ ያገናገኝችው የድሬዳዋ ከተማ በቅርቡ የድሬዳዋ ደዋሌ ምድር ባቡር ደርጅትን አስተዳደሩ በባለቤትነት ተረክቦ ማስተዳደር መጀመሩ እና በዚህም በርካታ የስራ እንቅስቃሴዎችን እያከናወነ መሆኑ ይታወቃል፡፡
    የምድር ባቡር ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አየለ ወ/ዮሀንስ በዛሬው እለት ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት የምድር ባቡር ድርጅት መጋቢት 24/2014 ዓ.ም የሚንስትሮች ምክር ቤት ባወጣው ደንብ መሠረት ተቋቁሞ በድሬደዋ አስተዳደር ስር እንዲሆን መወሰኑን ተከትሎ የምድር ባቡር ድርጅት ሰፊ የስራ እንቅስቃሴ በማድረግ ከድሬደዋ ደወሌ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልጸዋል፡፡
    ይህንን ሰራ ለማሳለጥም 4 ባቡሮች፣ 434 ጋሪዎችን ተዘጋጅተው ወደ ስራ እንዲገቡ የማድረግ ስራዎች ተሰርተው ከድሬዳዋ ደወሌ 208 ኪሎ ሜትር በመጓዝ በሳምንት ሁለት ቀን ጉዞ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡
    የምድር ባቡር ድርጅት ስራ መጀመር ለሰራተኛው ህልውናውን እንዲያገኝ ያደረገ ፤እንዲሁም ከፍተኛ የስራ መነቃቃትን የፈጠረ መሆኑን ያወሱት ሀላፊው በዚህም ለአስተዳደሩ ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሃር ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
    በድርጅቱ በተለያዩ የስራ መስክ የሚሰሩ 300 ሰራተኞች የሚገኙ ሲሆን ከግንቦት 1/2014 ጀምሮ የበረሀ አበል ክፍያ እንዲገኙ መደረጉንም አንስተዋል ፡፡
    በተጨማሪም የሰራተኛው በስራው ላይ ያለውን ከፍተኛ መነቃቃት መነሻ በማድረግ 10% ደሞዝ መጨመሩን ሀላፊው ተናግረዋል፡፡
    የድሬደዋ ደዋሌ ምድር ባቡር ድርጅት ለአስተዳደሩ በመወሰኑም በርካታ ጥቅም እንዳስገኝላቸውም ሃለፊው ያነሱ ሲሆን በተለይ ምድር ባቡሩ ተጠናክሮ ስራ በጀመረበት እንኳን በፊት 223ሺ (ሁለት መቶ ሀያ ሶስት) ብር ገቢ የሚያገኝ የነበረው አሁን 7 (ከሰባት መቶ ሺ) ብር በላይ በማግኝት ገቢውን ማሳደግ መቻሉን ገልጸዋል፡፡
    ድርጅቱ ለኢንዱስትሪው ዘርፍ ከፍተኛ አቅም ያለው በመሆኑን በአካባቢ ካሉ ኢንዱስተሪዎች ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችሉ ስራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡
    በቀጣይም ካርጎን ጨምሮ የባቡር ትራንስፖርት እንቅስቃሴውን በማጠናከር በኩል፤በቱሪዝሙ ዘርፍ ታሪክን የሚዘክሩበት የሚያውቁበት የመዝናኛ ትዕይንቶችን ከማድረግ አንስቶ የስልጠና ማዕከላት በመክፈት የማጠናከር ስራዎች እንዲሁም ተደራሽነትን በማስፋት የሲቲ ዞን የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች በቀጣይ ትኩረት ተደርጎ የሚሰራቸው ቁልፍ ተግባራ መሆኑን ሀላፊው አስረድተዋል፡፡
    በመጨረሻም የድሬደዋ ደወሌ ምድር ባቡር ድርጅት ለዚህ ስኬት መብቃት ከፍተኛ እገዛ ላደረጉ በአስተዳደሩ ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር የሚመራዉ የአሰተዳደሩ ካቢኔና መላዉ የአሰተዳደሩ ነዋሪ ምሰጋና አቅርበዋል ።