መነሻ ምክንያቱ እየተጣራ በሚገኘው በእዚሁ የእሳት ቃጠሎ በአንድ ሱቅ ላይ ሙሉ ለሙሉ እንዲሁም ሌሎች አምስት ሱቆች ላይ ደግሞ ቀላል የንብረት ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታውቋል ::
የድሬዳዋ ፖሊስ እንዳስታወቀው ትላንት ምሽት ሀምሌ 25 ቀን 2014 ዓ/ም ከምሽቱ በ 3:30 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 07 ክልል በሚገኘው የታይዋን የገበያ አዳራሽ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ የእሳት ቃጠሎ መከሰቱን ገልፆ በቃጠሎውም ግምቱ ለግዜው ያልታወቀ ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል ያለ ሲሆን ከድረሱት የንብረት ጉዳቶች ውስጥም፣በ 5 የልብስ መደብሮች ላይ ቀላል ጉዳት ሲደርስ አንድ የተለያዩ አልባሳት እና መገልገያ እቃዎች መሸጫ መደብርም ሙሉ ለሙሉ በቃጠሎው መውደሙን ፖሊስ አስታውቋል::
የእሳቱ ቃጠሎዉን ለመቆጣጠር የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የእሳት አደጋ አባላት ከቀጠናው የአፈተኢሳ ፖሊስ ጣቢያና የአድማ ብተና ፖሊስ እንዲሁም ከመላው ማህበረሰቡ ጋር በመሆን በሰጡት ፈጣን ምላሽ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ የተከሰተውን የእሳት ቃጠሎ ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር መቻሉንም ፖሊስ ገልፆል::
የድሬደዋ ፖሊስ ጨምሮም እንዳስታወቀው በቀጣይ ግዜያት የእሳት ቃጠሎውን መንስኤና የደረሰውን የጉዳት መጠን አጣርቶ ይፋ እንደሚያደርግ ገልፆል::


