በድሬዳዋ ታይዋን የገበያ አዳራሽ ትላንት ምሽት በደረሰ የእሳት ቃጠሎ በመሸጫ ሱቆች ላይ የንብረት ጉዳት መድረሱን ፖሊስ ገለፀ ::
መነሻ ምክንያቱ እየተጣራ በሚገኘው በእዚሁ የእሳት ቃጠሎ በአንድ ሱቅ ላይ ሙሉ ለሙሉ እንዲሁም ሌሎች አምስት ሱቆች ላይ ደግሞ ቀላል የንብረት ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታውቋል :: የድሬዳዋ ፖሊስ እንዳስታወቀው ትላንት ምሽት ሀምሌ 25 ቀን 2014 ዓ/ም ከምሽቱ በ 3:30 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 07 ክልል በሚገኘው የታይዋን የገበያ አዳራሽ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ የእሳት ቃጠሎ መከሰቱን…


