የ 2014 በጀት ዓመት ማጠቃለያ ምዕራፍ አጠቃላይ የስራ ክንውን ማጠቃለያ መድረክ በዛሬው እለት በኢትዮ-ኢጣሊ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሰብሰቢያ አዳራሽ የተካሄደ ሲሆን በዚሁም መድረክ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር በተጠናቀቀዉ የበጀት አመት እቅድ አፈጻጸም ጥሩ ዉጤት መገኘቱን አዉስተዉ ለተገኘዉ አመርቂ ዉጤት መላው አመራሮች ከጠባቂነት ስሜት ተላቀዉ በጊዜ የለኝም መንፈስ ስራዎችን በበላይነት በመምራት ለተገኘዉ አመርቂ ውጤት የሚጠበቅባቸዉን የአመራርነት ሚና ለተወጡ አመራሮች ምሰጋና ይገባቸዋል ብለዋል ። በቀጣይም የሚሰሩትን ማበረታታትና እዉቅና በመሰጠት ለተሻለ ውጤት የሚተጉ ብቁና ጠንካራ አመራር የማፍራት ሂደት ትኩረት የሚሰጠዉ ጉዳይ መሆኑን ክቡር ከንቲባዉ አብራርተዋል።
አመራሩ እያንዳንዱን ተግባር ሲፈጽም የፈጸመበትን አግባብ መገምገም ስላለበት ከዚህ ቀደም ከነበረው አይነት ሳይሆን በስራ አፈጻጸም ዉጤት ላይ ያተኮረ መርህን የተከተለ መሆን እንዳለበት በመግለጽ የአመራር አቅም ግንባታ ስልጠና ነክ ግምገማ እስከ ነሀሴ 9 / 2014 መጠቃለል እንዳለበት የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ገልጸዋል።
የማጠቃለያ ምዕራፍ የነበሩ አፈጻጸሞች አመራሩን ለመለካትና በመፈረጅ ለህዝቡ የገባነውን ቃል ለመፈጸም በቀጣይ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባና በአመቱ የተሻለ አፈጻጸም ላሳዩ ተቋማት ፣ ቀበሌዎችና ክላስተሮች እውቅናና ሽልማት እንደሚኖርም ክቡር አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ገልጸዋል።
የ2014 በጀት ዓመት ማጠቃለያ ዕቅድ አፈጻጸም የአመራርና የአባላት አቅም ማጎልበቻ ስልጠና ነክ ግምገማ ማስፈጸሚያ ሰነድ በብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ በሆኑት አቶ ሻኪር አህመድ ቀርቧል ።
በመጨረሻም የ2015 በጀት ዓመት እቅድ በሚመለከታቸው አካላት ተገቢው ውይይት በየደረጃው ከተደረገ በኃላ ለአፈፃፀሙ መላው አመራር እና ህዝባችን ለአፈፃፀሙ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ መድረኩ ተጠናቋል


