ኮርፖሬሽኑ በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር በመጀመሪያው ዙር ከሚገነባቸው የግንበታ ሳይቶች መካከል በሆነው ኢሚግሬሽን ሳይት ለሚገነባው ዘመናዊ ሕንጻ የግንባታ መሰረተ ድንጋይ በማስቀመጥ የግንባታ ሒደቱን አስጀምሯል፡፡
ኮርፖሬሽኑ በቀጣይ የሚገነባቸውን ግንባታዎችንም በተመለከተ የኮርፖሬሽኑ አመራሮች ከድሬደዋ ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጀዋር ፣የም/ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፈቲያ አደን፣ የአሰተዳደሩ ም/ከንቲባ ክቡር አቶ ሀርቢ ቡህ ፣የአሰተዳደሩ ም/ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ከሪማ አሊ እና ከሌሎች የ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡
ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሃር በውይይቱ ወቅት እንደተናገሩት ኮርፖሬሽኑ በአዲስ አበባ ከተማ እያካሄደ ካለው ውጤታማ የቤት ልማት ፕሮግራም ከተመለክትን በኋላ ኮርፖሬሽኑ በድሬደዋ ከተማም ግንባታ እንዲጀምር በጉጉት ስንጠብቅ ነበርም ብለዋል፡፡
አክለውም ኮርፖሬሽኑ በድሬደዋ ከተማ ለሚያካሂደው የቤት ልማት ፕሮግራም ከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲሚያደርግም ተናግረዋል፡፡
ቃል በገቡት መሰረት እንዲሁም የሳይቶቹ የግንባታ ሒደት እንዲጀመር ቀጥተኛ አመራር በመስጠት እና የቅርብ ክትትልና ድጋፍ እያደረጉ ላሉት ለኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማልና የኮርፖሬሽኑ አመራሮች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ከአራት ዓመታት በፊት የጀመረው ለውጥ በአዲስ አባባ ከተማ ብቻ ተወስኖ አለመቅረቱንና ይልቁንም ለአገራዊ ብልጽግና ጉዞችን ጭምር የሚተርፍ አቅም የፈጠረ ተቋም እየሆነ መምጣቱንና የድሬደዋን እድገት የሚያፋጥኑ የቤት ልማት እቅዶችን አቅዶ መነሳቱ የዚሁ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚችል ክቡር ከንቲባ ከድር አንስተዋል፡፡
በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ሊለሙ የሚችሉ አዋጭ የግንባታ ሳይቶች ላይ ኮርፖሬሽኑ ግንበታ እንዲያካሂድ አስተዳደሩ የሚጠበቅበትን ድጋፍ እንደሚያደርግም ሌሎች የውይይቱ ተሳታፊ አመራሮች አረጋግጠዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ በአዲስ አበባ ከተማ እያካሄደ ካለው ሰፋፊ የቤት ልማት ፕሮግራም በተጨማሪ በድሬደዋ ከተማም ሰፋፊ የቤት ልማት ፕሮግራም ማከናወን የሚያስችለውን ጥናት ያካሄደ ሲሆን ይሄንኑ ለማሳካት ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በትብብር ለመስራትም የሚያስችለውን የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት ላይ ይገኛል፡፡
በሌላ በኩል ኮርፖሬሽኑ በአሰተዳደሩ ዘመናዊ አገልግሎት መሰጠት የሚያሰችለዉን በድሬዳዋ ያሰገነባዉን ቢሮ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት አሰመሪቋል።


