ይህ ስልጠና ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ አስር ቀናት ለሁሉም አመራሮችና አባሎች እንደሚሰጥም ተገልፆል ።
በስልጠና ማስጀመሪያ መርህ ግብር ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ኮሚሽነር አለሙ መግራ ‘ለማህበረሰቡ የሚንሰጠው አገለግሎት ፈጠን እና ተደራሽ ከማደረግ ባለፈ መንግስት ያስቀመጠውን የአስር አመት ዕቅድ ላይ የፀጥታ ተቋማት ሚናን በመረዳትና በመገንዘብ እንደ ሀገር በተጀመሩ የዕድገት ጉዞ ላይ የበኩላችንን ድርሻ ለመወጣት እንዲቻል ታሳቢ ተደርጎ ስልጠናው መዘጋጀቱን ነው የተናገሩት ።
“አዲስ የህግ ማስከበር እይታ አዲስ አገራዊ እምርታ” በሚለው የተዘጋጀው ይሄው ስልጠና በርካታ ርዕሰ ጉዳዮችን በውስጡ እንደያዘ የተገለፁት ኮሚሽነር አለሙ መግራ ሁሉም የፖሊስ አመራርና አባላት የሚሰጠውን ስልጠና በትኩረት በመከታተል ከስልጠና ያገኙትን ዕውቀትና ግንዛቤ በቀጣይ ወደ ተግባር መለወጥ እንደሚጠበቅባቸውም አሳሰበዋል ።
የስልጠናው አጠቃላይ አስፈላጊነትና ሂደት በተመለከተ በመድረኩ በም/ኮሚሽነር መኦ ተሾመ እና ም/ኮሚሽነር ውብት በፍቃዱ ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን ይሄው ስልጠና ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ አስር ቀናት ለሁሉም ፖሊስ አመራሮችና አባሎችም የሚሰጥ ይሆናል ።
በዛሬው ስልጠና መጀመሪያ መርሀ ግብር የድ/ዳ ፖሊስ ስታፍ አባላት፣ የመልካ ጀብዱ፣የሳቢያንእና የሀሎሌ ፖሊስ ጣቢያ አመራርና አባላት ተሳታፊ ሆነዋል።


