2022
በድሬደዋ ለነዋሪው ማህበረሰብ 100 ግራም ዳቦ በሁለት ብር ዋጋ እየተሸጠ ነው
በድሬዳዋ ከተማ ኢንዱስትሪ መንደር በ18 ሚሊዮን ብር ካፒታል የተገነባው የኡሚ ዳቦ መጋገሪያ እና ዱ ቄት ፋብሪካ በከተማው ነዋሪ ላይ የሚታየውን የኑሮ ውድነት ለማስታገስ በዘጠኙም የከተማ ቀበሌ በዝቅተኛ ዋጋ ከአስተዳደሩ በተደረገለት የስንዴ ድጎማ ለህብረተሰቡ ዳቦ በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡ የኡሚ ዳቦ መ ጋገሪያና ዱቄት ፋብሪካ ባለቤትና ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልሀኪም ያሲን ከድሬዳዋ አስተዳደር በተገኘ ድጋፍ በ2013…
የ3ኛ ዙር የመስክ ምልከታ የድሬ ደዋ አስተዳደር ምክር ቤት የከተማ ልማት ኮንስትራክሽንና መዘጋጃቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በከተማ ስራ አስኪያጅ ቢሮ እየተሰሩ ያሉትን ፕሮጀክቶች ጎበኘ።
ቋሚ ኮሚቴው 7ኛው ቀን የመስክ ምልከታ በመንገዶች ባለስልጣንና ከተማ ፅዳትና ውበት ኤጄንሲ እየተሰሩ ያሉት በርካታ ፕሮጀክቶች የሉበትን ሁኔታ ስመለከት የነበረ ሲሆን ከአድሱ ኬላ እስከ ጂቡቲ ሀይ ዌይ የሚያደርስ በ521ሚሊየን ብር እየተሰራ ያለው የ4.2ኪ.ሜ መንገድ ግንባታው 13% መድረሱን ከሳይት ባለሞያዎችም ማረጋገጥ ችሏል። በተጨማሪም የቆሻሻ ማስወገጃ አከመባቢ የተቋቋመው የኮምፖስና ፕላስቲክ ምርት ሰራ ለይ 60 ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ…
በድሬዳዋ አስተዳደር እሁድ ጠዋት ለትራንስፖርት እንቅስቃሴ ዝግ እንዲሆን የተወሰነው ውሳኔ ላይ ማሻሻዮች ተደረገ ።
በድሬዳዋ አስተዳደር በሳምንቱ መጨረሻ እሁድ ላይ ከጠዋት 12 ሰአት እስከ 4 ሰአት ድረስ በከተማዋ ላይ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ዝግ ከመደረጉ ጋር ተያይዞ ከዚህ ቀደም በጉዳዩ ዙሪያ የተለያዩ ጥያቄዎች ሲነሱ ቆይተዋል ። በዚሁም ጉዳይ ዙሪያ ለመምክር በዛሬው እለት በራስ-ሆቴል መሰብሰብያ አዳራሽ ከሀይማኖት አባቶች ጋር ውይይት ተካሂዷል ። በተለይም እድሜያቸው የገፍ እናት አባቶች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እሁድ…
በሶማሌ እና አፋር ክልል አዋሳኝ ቀበሌዎች በተለያዩ ጊዜያት ሲከሰቱ የቆዩ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ሁለቱ ክልሎች ከስምምነት መድረሳቸውን አስታውቀዋል። ገዳማይቱ ፣ እንዱፎ እና ገርበኢሴ በተባሉ አዋሳኝ ቀበሌዎች ይከሰቱ ነበሩ ግጭቶች ሞት እና መፈናቀል ከማስከተል ባለፈ ሁለቱን ክልሎች የቃል እሰጣ አገባ ውስጥ ሲያስገባቸው ቆይቷል። የአፋር ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ጅግጅጋ ተገኝተው ከሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ እና ሌሎች ባለስልጣናት ጋር ውይይት አካሂደዋል። በውይይቱ ማጠቃለያም ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ያስችላል የተባለ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
Read More
ዘንድሮ በድሬዳዋ ለሚኪያሄደው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ቅድመ ዝግጅት እየተጠናቀቀ ነው::
በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ ለ4ተኛ ጊዜ ለሚኪያሄደው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ አበረታች የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ የደን ልማት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ተናግረዋል። በዋና ዳይሬክተሩ አቶ ከበደ ይማም የተመራ ቡድን ዛሬ ረፋድ ድሬዳዋ ተገኝቶ ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ የተገነባውን ዘመናዊ የችግኝ ማፍያ ጣቢያና ለዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ እየተካሄዱ የሚገኙትን እንቅስቃሴዎች ጎብኝቷል፡፡ በፌደራል መንግስት ድጋፍ በመላው አገሪቱ…
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የበጀት፣ ኢኮኖሚ፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እያደረገ ባለው የመስክ ምልከታው የድሬዳዋ አስተዳደር የአነስተኛና መካከለኛ መኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ክላስተር ልማት ኮርፖሬሽንን የስራ አፈፃፀም ገምግሟል።
ቋሚ ኮሚቴው በኮርፖሬሽኑ የተሰሩ በደበኛ ስራዎችን፣ ከዚህ በፊት በቋሚ ኮሚቴው የተሰጡ ግብረመልሶች እንዲሁም በህዝብ ውክልና የውይይት መደረኮች ኮርፖሬሽኑን በተመለከተ ከህዝብ የተነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ተቋሙ ያከናወናቸውን ተግባራት ገምግሟል። በዚሁ አግባብ ኮርፖሬሽኑ ያከናወናቸን ተግባራት በተመለከተ የአነስተኛና መካከለኛ መኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ክላስተር ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኡስማን አህመድ ለቋሚ ኮሚቴው ማብራሪያ ሰተዋል። አቶ ኡስማን በሰጡት…
በድሬዳዋ “ለፍቅር እሮጣለሁ” የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር እየተካሄደ ነው በድሬደዋ በርካታ አላማዎች ያነገበ “ለፍቅር እሮጣለሁ” የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር እየተካሄደ ይገኛል።
ውድድሩ የድሬዳዋ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን በኮማንደር አትሌት ጌጤ ዋሚ ከሚመራው ሂማ ሬስ ኢንተርናሽናል ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው። በሺዎች የሚገመቱ የድሬዳዋ ነዋሪዎች እና የአገራችን ታዋቂ አትሌቶች የተሳተፉበትን የ10ሺ እና የ5ሺ ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ ያስጀመሩት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር፣ ታዋቂዋ አትሌት ኮማንደር ጌጤ ዋሚ፣ የአስተዳደሩ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ፊራንኦል ቡልቻ ሌሎች በርካታ እንግዶች ናቸው።…


