በድሬዳዋ ከተማ ኢንዱስትሪ መንደር በ18 ሚሊዮን ብር ካፒታል የተገነባው የኡሚ ዳቦ መጋገሪያ እና ዱ ቄት ፋብሪካ በከተማው ነዋሪ ላይ የሚታየውን የኑሮ ውድነት ለማስታገስ በዘጠኙም የከተማ ቀበሌ በዝቅተኛ ዋጋ ከአስተዳደሩ በተደረገለት የስንዴ ድጎማ ለህብረተሰቡ ዳቦ በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡
የኡሚ ዳቦ መ ጋገሪያና ዱቄት ፋብሪካ ባለቤትና ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልሀኪም ያሲን ከድሬዳዋ አስተዳደር በተገኘ ድጋፍ በ2013 ዓ/ም በ18 ሚሊዮን ብር ካፒታል የተቋቋመ እና በከተማው በ13 የተለያዩ አካባቢዋች ሱቆችን በመክፈት በቀን 190,800 ዳቦ በማከፋፈል ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
በአሁን ሰዓት ፋብሪካው ሁለት ማሽን ተተክሎለት ዳቦ በመጋገር ላይ እንደሚገኝ የገለፁት የፋብሪካው ዳይሬክተር ለ68 ቋሚና ጊዜያዊ ሠራተኞች የሥራ እድል መፈጠሩንና በቀጣይ በዘጠኙም ከተማና የገጠር ቀበሌዎች የዳቦ ተደራሽነትን ለማስፋት በመስራት ላይ እንዲሚገኙ በመግለፅ በቀጣይ አስተዳደሩ ባዘጋጀላቸው የመሸጫ ሱቆች በመጀመር ነዋሪውን ህብረተሰብ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እናደርጋለን ብለዋል፡፡
ኃላፊው አያይዘውም መንግስት ባደረገላቸው የስንዴ ድጎማ ፋብሪካው በቀን 190,800 ዳቦ በቀን የሚያመርት መሆኑንና በቀጣይ በቀን 750,000 ዳቦ ለማምረት እየተሰራ መሆኑንና በቅርብ ጊዜ በመልካ ጀብዱ የዳቦ መ ጋገሪያ ማሽን ተከላ እንደሚካሄድና ለአካባቢው የገጠር ቀበሌዎች ተደራሽ እንደሚደረግ አስረድተዋል፡፡
( ግንቦት10/2014 ዓ.ም.)


