ቋሚ ኮሚቴው 7ኛው ቀን የመስክ ምልከታ በመንገዶች ባለስልጣንና ከተማ ፅዳትና ውበት ኤጄንሲ እየተሰሩ ያሉት በርካታ ፕሮጀክቶች የሉበትን ሁኔታ ስመለከት የነበረ ሲሆን ከአድሱ ኬላ እስከ ጂቡቲ ሀይ ዌይ የሚያደርስ በ521ሚሊየን ብር እየተሰራ ያለው የ4.2ኪ.ሜ መንገድ ግንባታው 13% መድረሱን ከሳይት ባለሞያዎችም ማረጋገጥ ችሏል።
በተጨማሪም የቆሻሻ ማስወገጃ አከመባቢ የተቋቋመው የኮምፖስና ፕላስቲክ ምርት ሰራ ለይ 60 ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ እድል የፈጠረ ሼድ ፣ በ2 ሚሊየን ብር ወጪ 2 ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት የበቃ 53 ሜትር የሚሆን የኮነክሪት መንገድ፣ ከ3 ሚሊየን ብር በላይ የወጣበት የደቻቱ ድልድይ እድሳትና የማሰዋብ ስራዎችና በድልድዩ ላይ እየተሰሩ ያሉት መብራትና የጓርደር ብረቶችች ስራዎችንም ተመልክቷል።
ቋሚ ኮሚቴው የመስክ ምልከታ ሲያደርግ በእነዚህ ፕሮጀክቶች ላይ የተሰማሩ ተቋራጮች፣ አሰፈፃሚዎች፣ ባለሞያዎችና ሰራተኞችን በማነጋገር አስፈላጊውን መረጃዎችንና በስራው ላይ ስላጋጠሟቸው ችግሮችንም አድምጧል።
በተለይም ከሚወገዱት ቆሻሻው ለይ የኮምፖስ ማዳበሪያና የፕላስቲክ ምርት ላይ ተሰማርተው ያሉት ወጣቶች ለ6 ወራት ያክል ጊዜ የገበያ ትስስር ባለማግኘት ምክንያት መቸገራቸውን ኮሚቴው በምልታው አረጋግጧል።


