የ3ኛ ዙር የመስክ ምልከታ የድሬ ደዋ አስተዳደር ምክር ቤት የከተማ ልማት ኮንስትራክሽንና መዘጋጃቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በከተማ ስራ አስኪያጅ ቢሮ እየተሰሩ ያሉትን ፕሮጀክቶች ጎበኘ።
ቋሚ ኮሚቴው 7ኛው ቀን የመስክ ምልከታ በመንገዶች ባለስልጣንና ከተማ ፅዳትና ውበት ኤጄንሲ እየተሰሩ ያሉት በርካታ ፕሮጀክቶች የሉበትን ሁኔታ ስመለከት የነበረ ሲሆን ከአድሱ ኬላ እስከ ጂቡቲ ሀይ ዌይ የሚያደርስ በ521ሚሊየን ብር እየተሰራ ያለው የ4.2ኪ.ሜ መንገድ ግንባታው 13% መድረሱን ከሳይት ባለሞያዎችም ማረጋገጥ ችሏል። በተጨማሪም የቆሻሻ ማስወገጃ አከመባቢ የተቋቋመው የኮምፖስና ፕላስቲክ ምርት ሰራ ለይ 60 ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ…


