ቋሚ ኮሚቴው በኮርፖሬሽኑ የተሰሩ በደበኛ ስራዎችን፣ ከዚህ በፊት በቋሚ ኮሚቴው የተሰጡ ግብረመልሶች እንዲሁም በህዝብ ውክልና የውይይት መደረኮች ኮርፖሬሽኑን በተመለከተ ከህዝብ የተነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ተቋሙ ያከናወናቸውን ተግባራት ገምግሟል።
በዚሁ አግባብ ኮርፖሬሽኑ ያከናወናቸን ተግባራት በተመለከተ የአነስተኛና መካከለኛ መኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ክላስተር ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኡስማን አህመድ ለቋሚ ኮሚቴው ማብራሪያ ሰተዋል።
አቶ ኡስማን በሰጡት ማብራሪያም የመሰረተ ልማት አቅርቦትን ከማሻሻል አንፃር በኢንዱስትሪ መንደር ሳይት በአዲስ ተገንብተው ላለቁ ማምረቻ ሼዶች አዲስ የውሃ መስመር ለማስገባት ዋጋ በማስገመትና ክፍያ በመክፈል ለሼዶቹ አዲስ የውሃ መስመር ዝርጋታ መዘርጋት መቻሉን ለቋሚ ኮሚቴው አስረድተዋል፡፡
በኦክስፋም ገበያ ማእከል፣በገንደ ገበሬ ገበያ ማእከል ፣በዲፖ ገበያ ማእከል ካፍቴሪያ፣ በሰፈረሰላም ዶሮ ቤት ፣በመልካ የማምረቻ ማእከል ፤ በመጋላ ህንጻ እንዲሁም በኮካ ገበያ ማእከል አዲስ የውሀ መስመር ዝርጋታ የተከናወነ ሲሆን በመጋላ ገበያ ማዕከል ችግር የነበረበትን የመጸዳጃ ቤት መስመር የመጠገን እንዲሁም የሮቶ ውሃ መስመር ዝርጋታ በመስራት ህንፃውን የውሃ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለም ነው አቶ ኡስማን የገለፁት፡፡
ከዚህም ባሻገር የመ/ጀብዱ ሳይት መፀዳጃ ቤት ያለበትን ውዝፍ ክፍያ በመክፈል የውሃ አገልግሎት ተጠቃሚ የተደረገ ሲሆን በኢንዱስትሪ መንደር አዲስ ለተሰሩት እና ግንባታቸው ለተጠናቀቁት ስድስት ሼዶች የ1250KVA ትራንስፎርመር እንዲገባ የኤሌክትሪካል ዲዛይን የመስራት እና የGeneral Line ግምት በማስገመት የግምት ዋጋ ማሰራት የተቻለ ሲሆን ቅድሚያ ለተሰሩት ስድስት ሼዶች የ1250KVA ትራንስፎርመር እንዲገባ የMV መስመር እንዲዘረጋ መደረጉን ቋሚ ኮሚቴው በመስክ ምልከታው አይቷል።
ኮርፖሬሽኑ አዲስ የተረከበው የጎሮ የገበያ ማዕከልን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ የ100KVA ትራንስፎርመር የኤሌክትሪክ ዲዛይን በመስራት እና በማስገመት የግምት ሂሳብ ማሰራቱን ለቋሚ ኮሚቴው የገለፀ ሲሆን በኢንዱስትሪ መንደር ከሚገኙ ከነባር ሼዶች መካከል ወደ ስራ ለገቡት ሁለት አምራች ኢንደስትሪያሊስቶች በሚያስፈልጋቸው የሀይል ፍጆታ መሰረት የ Active Reactive ቆጣሪ እንዲገባላቸው መደረጉን አቶ ኡስማን ገልፀዋል።
ከመሰረተ ልማት አቅርቦትና አጠቃቀም ጋር ያሉ መረጃዎችን ከማሰባሰብ አንፃር ኮርፖሬሽኑ በስሩ የሚያስተዳድራቸው ማምረቻ እና መሸጫ ማዕከላት (ከኢንዱስትሪ ሳይት ውጪ) ያለባቸውን የውሃ አገልግሎት ውዝፍ ክፍያ ከውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ጋር በመተባበርና በመለየት የየሳይቶቹን የክፍያ መጠን የማውጣት ስራ የተከናወነ ሲሆን በዚሁ አግባብ ሳይቶቹ ያሉባቸውን የውሀ አገልግሎት ውዝፍ ክፍያን የማጣራት ስራው ከ70% በላይ መጠናቀቁን እና በቀጣይም በኢንዱስትሪ መንደር እና በሌሎች ሳይቶች ያሉ ውዝፍ ክፍያዎችን የማጥራት ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና ስራ አስኪያደፈጁ ለቋሚ ኮሚቴው አስረድተዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ግንባታቸው በሂደት ላይ የሚገኙ ማዕከላትን ከመከታተልና ከመደገፍ አንፃር የግንባታ ስራቸው በሂደት ላይ የሚገኙትን የማኑፋክቸሪንግ ሼዶች ውስጥ የG+4 ህንጻ ግንባታን በተከታይነት
የመደገፍ እነደሁም ለG+4 የሚሆኑ ያልተሟሉ ዲዛይኖችን በማሟላት ስራዎቹ በአግባቡ እንዲቀጥሉ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በኢንዱስትሪ መንደር ለተገነባው የማምረቻ ሼድ ማዕከልም የአጥር፤ የመጸዳጃ ቤት፤ የሻወር ቤት ፤የካፌ እና የዋና በር ግንባታ ስራዎች በእቅዳቸው መሰረት እዲጠናቀቁ የመከታተልና የመደገፍ ስራ ማከናወኑም ተመላክቷል።
ከዚህም ባሻገር በኢንዱስትሪ የተገነቡ ማምረቻ ሼዶች የተሰሩላቸውን የሳኒተሪ መስመሮች በመፈተሸ ከፊል ርክክብ መከናወኑን እና የማንሆል እና የሴፕቲክ ታንክ ግንባታም መጀመሩን ቋሚ ኮሚቴ በመስክ ምልከታው ማየት የቻለ ሲሆን በተለይም ለተጠቃሚዎች የተላለፉ የማምረቻ እና መሸጫ ሼዶችን መሰረተ ልማቶች በአግባቡ ከመጠቀም አንፃር ውስንነቶች መኖራቸውን በመግለፅ በቀጣይም ኮርፖሬሽኑ አሁን ያሉትን ጠንካራ አፈፃፀሞች በማስቀጠል ለተሻለ አፈፃፀም እንዲሰራ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የበጀት፣ ኢኮኖሚ፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ አይናለም ተዘራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡


