የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የበጀት፣ ኢኮኖሚ፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እያደረገ ባለው የመስክ ምልከታው የድሬዳዋ አስተዳደር የአነስተኛና መካከለኛ መኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ክላስተር ልማት ኮርፖሬሽንን የስራ አፈፃፀም ገምግሟል።
ቋሚ ኮሚቴው በኮርፖሬሽኑ የተሰሩ በደበኛ ስራዎችን፣ ከዚህ በፊት በቋሚ ኮሚቴው የተሰጡ ግብረመልሶች እንዲሁም በህዝብ ውክልና የውይይት መደረኮች ኮርፖሬሽኑን በተመለከተ ከህዝብ የተነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ተቋሙ ያከናወናቸውን ተግባራት ገምግሟል። በዚሁ አግባብ ኮርፖሬሽኑ ያከናወናቸን ተግባራት በተመለከተ የአነስተኛና መካከለኛ መኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ክላስተር ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኡስማን አህመድ ለቋሚ ኮሚቴው ማብራሪያ ሰተዋል። አቶ ኡስማን በሰጡት…


