ዲዛይነር ሳራ መሀመድ ለ 5 መቶ ህጻን ተማሪዎች የዩኒፎርም ድጋፍ አደረገች ለምስራቅ ጀግኖች አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ለከዚራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ባጠቃላይ ለአምስት መቶ ለሚሆኑ ህጻን ተማሪዎች በዛሬው እለት በምክትል ከንቲባው ቢሮ ውስጥ ድጋፍ ተደረገ፡፡
በድጋፍ ስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ እንደተናገሩት ዲዛይነር ሳራ እያደረገች ላለው ድጋፍ በራሳቸውና በትምህርት ማህበረሰቡ ስም አመስግነው ለ500 ለተማሪዎቹ ሙሉ ዩኒፎርም ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋ፡፡ አንድም ተማሪ በትምህርት ቁሳቁስ ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው መቅረት የለባቸውም ብለን አቅደን ከምንቀሳቀስባቸው አንዱ ከደብተርና ከብዕር ባለፈ ዩኒፎርም ለሌለው ተማሪ ድጋፍ ማሰባሰብ ነው፤…


