የተመድ የሰብዓዊ መብት የባለሙያዎች ኮሚሽን ያወጣው ሪፖርት ወገንተኝነቱን እና የተሰጠውን ፖለቲካዊ ተልዕኮ ለማሳካት በሚያስቸለው መልኩ የተዘጋጀ መሆኑን የሚጠቁሙ የሪፖርቱ ነጥቦች::
ሪፖርቱን ያዘጋጀው ኮሚቴ የተቋቋመው ፖለቲካዊ ፍላጎት ያላቸውን ሀገራት እና ተቋማት ጥቅም ለማስጠበቅ መሆኑን ከሚያመላክቱ የሪፖርቱ ክፍሎች እና መሰረታዊ ስህተቶች መካከል ሉዓላዊት በሆነች ሀገር እና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት የተፈረጀን የሽብር ቡድን “የትግራይ ሀይሎች” “የትግራይ ሰራዊት” በሚል የክብር ስም መጥራቱ፤ ገለልተኛ መሆን የሚያስችለው ቁመናም ያለው አለመሆኑ፤ ኮሚቴው ይህን ሪፖርት ሲያዘጋጅ የሽብር ቡድኑ ሁነኛ መገለጫ የሆኑትን…


