ዛሬ መስከረም 10/2015 ዓ.ም የድሬደዋ ደወሌ ሁሉም የቦርድ አባላት እና የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ አቶ ከድር ጁሀር በተገኙበት የሁለት ወር ሪፖርት ግምገማ ላይ የተከናወኑ ተግባራት በዝርዝር የቀረቡ ሲሆን በአፈፃፀሙም የሚከተሉት ዋናዋና አፈፃፀሞች እንደሚከተለው ቀርበዋል በዚሁም መሰረት 1.በሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ለድሬዳዋ አስተዳደር የተላለፈው የተቋሙ ንብረቶች ርክክብ፤ በገንዘብ ሚኒስቴር አረካካቢ ቡድን አማካኝነት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።
2. በባቡር ትራንስፖርት የመንገደኞች ቁጥር፣ የጭነት ማጓጓዝ አቅም እና የተቋሙ ገቢ እድገት ከማሳየቱ በተጨማሪ፤ በቴክኒክ ክፍሎች አማካኝነት በአስተዳደሩ ስር ለሚገኙ መንግስታዊ ተቋማት፤ የቴክኒክ እገዛና ድጋፍ መስጠት እንደተጀመረ ተገልጿል።
3.የምድር ባቡር ድርጅቱን ለቱሪስት እና ለመዝናኛነት ምቹ ለማድረግ፤ በተቋሙ ውስጥ የሚገኙ ስፍራዎች የተለዩ ሲሆን፤ የግቢውን የራኬት ሐዲድ፣ የሎኰሞቲቭና የተጎታች ጋሪዎች፣ እንዲሁም በጎርፍ የተጎዱ ሐዲዶችን የመጠገን ስራ እንደተከናወነ በሪፖርቱ ተጠቅሷል።
በመጨረሻም የቦርዱ ሰብሳቢ እና የአስተዳደሩ ም/ከንቲባ የተከበሩ አቶ ሀርቢ ቡህ በማጠቃለያቸው በአሁኑ ወቅት 281 ሠራተኞች ያሉት የድሬዳዋ – ደወሌ ምድር ባቡር ድርጅት፤ ለድሬዳዋ አስተዳደር ከተሰጠ ወዲህ ለሠራተኞች የበረሀ አበል እና 10% የደመወዝ ጭማሪ የተደረገ ሲሆን፤ በቀጣይ ያሉበትን ውስንነቶች በመቅረፍ የድሬዳዋ መታወቂያነቱን ማስመስከር እንደሚገባው የተቋሙ የቦርድ አባላት አሳስበዋል፡፡


