የድጋፍ ስነስርዓቱን በማስመልከት የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ከሪማ አሊ በደረጉት መክፈቻ ንግግር ምክር ቤቱ የህዝብ እንደራሴ በመሆኑ የህብረተሰቡን መህበራዊ ችግሮች በመለየት ልዩ ልዩ ድጋፎችን እንደሚየደርግ ገልጸዋል፡፡ በዚሁ መሰረት በአስተዳደሩ የሚገኙ አነስተኛ ገቢ የለቸው ቤተሰብ ልጆች ከትምህርት ገበታቸው በመማሪያ ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት እንዳይቀሩ ምክር ቤቱ ይህንን ድጋፍ ማድረጉን አስረድቷል፡፡በመቀጠል የድሬደዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ የተከበሩ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ በምክር ቤቱ የተደረገውን ድጋፍ በመመስገን የትምህርት ጉዳይ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች የሚመለከት በመሆኑ ሌሎች ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንደለበት ገልጸዋል፡፡
የድጋፍ ስነስርኣቱ ላይ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ሰቢሳቢዎች፣በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የድሬደዋ አስተዳደር ተወካይ የተከበሩ ዶክተር ቢፍቱ መሀመድ ፣የድሬደዋ አስተዳደር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ የተከበሩ ወ/ሮ ጫልቱ ሁሴን፣የምክር ቤቱን ጸሀፊ ጨምሮ ሌሎች የቁሳቁስ ድጋፍ የደረጉ፣ የአስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ በለሙያዎች፣የተማሪ ወላጆች፣ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የመጡ ተማሪዎች በድጋፍ ስነስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።
በመጨረሻም የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን ባስተላለፉት መልእክት “ተማሪን መርዳት ለነገ ሀገር እድገት መሰረት መጣል ነው” በማለት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ የተደረገላቸዉን ተማሪዎች በትምህርት ቁሳቁስ እጦት ምክንያት አንድም ተማሪ ከትምህርት ገበታው እንዳይቀር ድጋፍ መደረጉን ገልፀው ተማሪዎች ትምህርታቸዉን ጠንክረዉ በመማርና፤ወላጆቻቸዉን የሚወዱና የሚያከብሩ ለሀገር የሚጠቅሙ መሆን እንዳለባቸውና መምህራንም እኛን ለዚህ እንዳበቃችሁን የትምህርት ጥራትን በማስጠበቅና ነገ ላይ ሀገር ወዳድ ትዉልድ እንድናገኝ ተማሪዎች በስነምግባር የታነጹ እንዲሆኑ የበኩላችሁን እንድትወጡ በማለት ከአደራ ጭምር መልዕክተቸውን በማስተላለፍ ይህንን መልካም ስራ በተለያዩ ሁኔታዎች በማገዝ ድጋፋቸውን ለደረጉት አካላት በምክር ቤቱና በአስተዳደሩ ህብረተሰብ ስም ለቅ የለ ምስጋነቸውን የተከበሩ አፈ ጉባኤ ፈቲህያ አደን አቅርበዋል፡፡በቀጣይም ድጋፍ የተደረገላቸው ተማሪዎች ጥሩ ውጤት እና ደረጃ ላይ እንድደርሱ ወለጆችም የበኩላቸውን ክትትል እንድያደርጉ በማለት መልእክት በማስተላላፍ ለተማሪዎች ድጋፍ የተዘጋጀውን የትምህርት ቁሳቁስ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የድሬዳዋ አስተዳደር ተወካይ የተከበሩ ደክተር ቢፍቱ መሀመድ ጋር በመሆን ለአስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ አስረክበዋል፡፡
C @ ም/ቤት ህዝብ ግንኙነት ክፍል


