ይህን ያሉት የድሬዳዋ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ብሩክ ፈለቀ በዛሬው እለት በኮሙኒኬሽን ቢሮ አዘጋጅነት በአስተዳደሩ ለሚገኙ የሴክተር መስሪያ ቤቶች እና በዘጠኙም የከተማ ቀበሌዎች እንዲሁም በገጠር ክላስተሮች ላሉ ኮሙዩኒኬተሮች በተዘጋጀ ስልጠና ላይ ነው።
በድሬዳዋ አስተዳደር ለሚገኙ ኮሙዩኒኬተሮች በቀውስ ጊዜ ኮሚዩኒኬሽን ስትራቴጂ ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰቷል።
የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ብሩክ ፈለቀ ባስተላለፉት መልዕክት እንደተናገሩት ወጥነት ያለው የኮሚዩኒኬሽን ስርዓት በመዘርጋት በማህበራዊ ሚዲያዋች የሚነፈሱ የተዛቡ መረጃዋችን በቲክኖሎጂው በመታገዝ በሀገራችን የቀውስ ጊዜ ኮሚዩኒኬሽን መረጃ ፍሰቱ እውነታ የያዘ መረጃ ለማህበረሰቡ ማድረስ ይኖርብናል ብለዋል።
በቀጣይም እንደዚህ አይነት መሰል የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም የቢሮው ኃላፊ አቶ ብሩክ ፈለቀ ተናግረዋል።
በመድረኩም የ2015 ዓ.ም የዝግጅት ምዕራፍ የእቅድ ኦረንቴሽን ለቢሮ ሰራተኞች እና ባለድርሻ አካላት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
የስልጠናው ተሳታፊዎችም በሰጡት አስተያየት እንዲህ አይነት መድረኮች ቀጣይነት እንዲኖራቸውና ከቢሮው ጋር ያላቸው የግንኙነት አግባብ በተጠናከረ መልኩ ቢቀጥል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰተዋል።
በትዕግስት ቶሎሳ
ፎቶ፦በሰላም አበበ


