የተመድ የሰብዓዊ መብት የባለሙያዎች ኮሚሽን ያወጣው ሪፖርት ወገንተኝነቱን እና የተሰጠውን ፖለቲካዊ ተልዕኮ ለማሳካት በሚያስቸለው መልኩ የተዘጋጀ መሆኑን የሚጠቁሙ የሪፖርቱ ነጥቦች::

    • ሪፖርቱን ያዘጋጀው ኮሚቴ የተቋቋመው ፖለቲካዊ ፍላጎት ያላቸውን ሀገራት እና ተቋማት ጥቅም ለማስጠበቅ መሆኑን ከሚያመላክቱ የሪፖርቱ ክፍሎች እና መሰረታዊ ስህተቶች መካከል ሉዓላዊት በሆነች ሀገር እና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት የተፈረጀን የሽብር ቡድን “የትግራይ ሀይሎች” “የትግራይ ሰራዊት” በሚል የክብር ስም መጥራቱ፤ ገለልተኛ መሆን የሚያስችለው ቁመናም ያለው አለመሆኑ፤
    •  ኮሚቴው ይህን ሪፖርት ሲያዘጋጅ የሽብር ቡድኑ ሁነኛ መገለጫ የሆኑትን የጅምላ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ዘረፋ እና የንብረት ውድመት መፈጸምን በበርካታ ሰላም በራቃቸው የግጭት ቀጣናዎች እና ሀገራት ጭምር በመሰማራት በነበረው እና ባለው የሰላም ማስከበር ተሳትፎ እና ብቃት ጭምር ይህ ጥናት ከህግ እና ከአሰራር ውጪ በድጋሚ እንዲጠናለት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ጭምር በወታደራዊ ስነ-ምግባሩ፣ በግዳጅ አፈጻጸም ብቃቱ፣ በህዝባዊነቱ እና በተላበሰው የወገናዊነት ባህሪው ተደጋጋሚ ምስጋና እና እውቅና ሲቸረው ለቆየው ለኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት መስጠቱ፤
    •  የሰብዓዊ መብት ጥሰትን እንዲመረምር የተደራጀው ቡድን የተከተለው የጥናት አካሄድ ስህተት ያለበት ከመሆኑም በተጨማሪ የሰብዓዊ መብት ጥሰትን በቁጥር ላይ ተመስርቶ ስሁት ትንታኔ እና ብያኔ መስጠቱ እንዲሁም ቀደም ባሉት ጊዜያት ራሱ የሽብር ቡድኑ ያመነውን የጅመላ ጥፋት ክዶ እልፍ ሲልም ደግሞ በመጠቀም በአማራ እና በአፋር ክልሎች በሽብር ቡድኑ የተፈጸሙት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በትግራይ ክልል ከተፈጸመው ያንሳል በማለት በሰብዓዊነት ላይ የቀለደ ተልካሻ ሪፖርት ማዘጋጀቱ፤
    •  የሽብር ቡድኑን ሀሰተኛ መረጃዎች ስታስተጋባ የቆየችው የባለሙያዎች ምርመራ ቡድን አባሏ ካሪ ሙሩንጊን በኮሚሽነርነት መመደቡ ለዚህም ሴትየዋ ቀደም ባሉት ጊዜያት በሽብር ቡድኑ ሲሰራጩ የነበሩ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት አጋርነቷን ስትገለጽ መቆየቷን ከግል የቲውተር አካውነቶቿ የተገኙት መረጃዎች መጠቆማቸው፤
    •  ቀደም ሲል በተመድ የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽ/ቤት እና በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በጋራ የተጠናውን የጥናት ውጤት እና ምክረ-ሃሳብ ለመጠቀም ፈቃደኛ አለመሆኑ፤
    •  መንግስት በጋራ ኮሚሽኖቹ የጥናት ምክረ-ሃሳብ ላይ ተመስርቶ ያቋቋመው የሚኒስትሮች ግብረ ሃይል የምርመራ እና የክስ ኮሚቴ በአማራና በአፋር ክልሎች ያከናወነውን ጥናት እና ያገኘውን ውጤት እንዲሁም ያስቀመጠውን ምክረ-ሃሳብ በግብዓትነት ለመጠቀም ፈቃደኛ አለመሆኑ፤
    •  በትግራይ ክልል ተፈጸመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲያረጋግጡለት በመረጃ ምንጭነት የተጠቀማቸው ሰዎች የሽብር ቡድኑ አባላት፣ ታጣቂዎች፣ ፖለቲካዊ አመራሮች፣ ችግሩ ከመፈጠሩ አስቀድሞ ጭምር የፌዴራል መንግስትን ሉዓላዊ ሀገራዊ ስልጣንና ሀላፊነት በማጣጣልና በማዛባት ጭምር ለሽብር ቡድኑ ድጋፍ እና ከለላ ሲሰጡ የነበሩ ካድሬ የህክምና ባለሙያዎች፣ በክልል በሚገኙ የከፍተኛ ትመህርት ተቋማት አመራሮች እና ስመ መምህራን መሆናቸው፤
    • የምርመራ ውጤቱን ታማኝ እንዳይሆን ካደረጉት ምክንያቶች መካከል ለምርመራው ትክክለኛ የመረጃ ምንጮችን ሳይጠቅስ ከታማኝ ምንጮቼ ባሰባሰብኩት አስተማማኝ መረጃ በሚል የተለመደ የማወናበጃ ስልት መጠቀሙ ለወገንተኝነቱ አይነተኛ ማሳያ ሆኖ የሚቀርብ ነዉ