ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ

    የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያና ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ:-
    2014/15 የኢትዮ ዩኒቨርሲቲ መግቢያና
    የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ወደ ተመደቡበት ካምፖስ ጉዞ ሲያደርጉ #መያዝ #የተፈቀደላቸው፣#መያዝ #የተከለከሉ እና #የጊዜ #ሠሌዳ እንደሚከተለው ያለው ሲሆን ተማሪዎች ከወዲሁ ራሣችሁን እንድታዘጋጁ ይሁን።
    ❶#መያዝ #የተፈቀደላቸው
    ✡️አንሶላ፣
    ✡️ትራስ ጨርቅ፣
    ✡️የማታ ልብስ፣
    ✡️ደረቅ ምግብ፣
    ✡️ልብስ፣ቦርሳ፣
    ✡️የመፈተኛ ካርድ፣እርሳስ፣ላጲስ፣የማስታወሻ ደብተር፣ባዶ ወረቀት፤መጽሐፍ
    ❷፣#መያዝ #የተከለከሉ
    ☸️ማንኛውም ድምፅ የሚቀዳ፤ቪዲዮ የሚቀዳ ወይም ፎቶግራፍ የሚያነሳ፤
    ☸️ካሜራ
    ☸️ማንኛውም ከቴሌ መስመርም ይሁን ከቴሌ ውጭ መልዕክት በድጂታል ቴክኖሎጂ መቀበያ ወይም ማስተላለፊያ ውጤቶች(ታብሌት፣ኮሚፕዩተር፣ላብቶፕ፣ ስልክ፣አይፓድ፥ሃርድ ዲስክ፣ፍላሽ)
    ❸ #የጊዜ #ሠሌዳ
    ✡️ማህበራዊ ሳይንስ $social science dep’t
    ➤26_28/1/2015 ዩኒቨርስቲ መግቢያ
    ➤29/01/2015 ኦሬንተሽን
    ➤30/01/2015_02/02/2015 ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ ይሆናል።
    ✡️የተፈጥሮ ሳይንስ Natural Science dep’t
    ➤05_06/2/2015 ዩኒቨርስቲ መግቢያ
    ➤07/02/2015 ኦሬንተሽን
    ➤08/02/2015_11/02/2015 ፈተናው
    የሚሰጥበት ጊዜ ይሆናል።
    ትምህርት ሚኒስቴር