ለሁለተኛ ዙር የተደረገው ድጋፍ ከአስተዳደሩ ባለሀብቶችና ነዋሪዎች እንዲሁም የመንግስት ሰራተኞች ሲሆን ድጋፉ እስከ ጦርነቱ ፍጻሜ እንደሚቀጥል በቢሾፍቱ ባስረከቡበት ወቅት ተገልጿል።
የድሬደዋ አስተዳደሩ ለሀገር መከላከያ ደጀንነት ያረጋገጠበትን የስንቅ ድጋፍ ተገኝቶ ያስረከበ ሲሆን በርክክቡ ላይ የአስተዳደሩ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ የአስተዳደሩ ገንዘብና ኢኮነሚ ልማት ቢሮና የአስተዳደሩ ብልፅግና ፅ/ቤት ምክትል ሀላፊ ተገኝተዋል።


