የትምህርት ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ በእመቤታችን ጀምሮ ሳቢያን ቁ.2 ት/ቤት እንዲሁም በምስለ እናት ት/ቤት የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ ፣ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ አቡበከር አዶሽ እንዲሁም የማህበራዊ ዘርፍ የከንቲባው አማካሪ አቶ ዑመር አህመድ በጋራ በመሆን በት/ቤቶች የአጀማመር ሂደቱን በመስክ ምልከታ የተደረገበት ነበር፡፡
በ2015 ዓመት የትምህርት ዘመን 6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፣የ8ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ እንዲሁም 12ኛ ክፍል የሁለተኛ ደረጃ የማጠቃለያ ፈተና ይሰጣል ፡፡
በ2015 የትምህርት ዘመን ላይ ወደ ሙሉ ትግበራ የሚገባው አዲሱ ስርዓተ ትምህርት የጥራት ደረጃውን ጠብቆ እንዲተገበር በተለይ የግል እና መንግስታዊ ያልሆኑ ትምህርት ተቋማት ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ለማድረግ እና ከዚህ ቀደም በስርዓተ ትምህርት ትግበራ ላይ የነበሩ ጉድለቶችን ለማረም በጋራ መሰራት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።


