የኢትዮ-ፈረንሳይ የድንገተኛ አደጋ ህክምና ማዕከል እለት ተመረቀ ።
በድሬዳዋ አስተዳደር ያለውን የድንገተኛ አደጋ የህክምና አገልግሎትን በከፍተኛ ደረጃ ያሻሽለዋል ተብሎ የታመነውና በድሬዳዋ አስተዳደርና በጤና ሚኒስቴር በተመደበ 15 ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ ለድንገተኛ አደጋ አስፈላጊውን የሆነ የህክምና አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ የህክምና መሳሪያዎችና የጤና ባለሞያዎችን ያሟላው የኢትዮ-ፈረንሳይ የድንገተኛ አደጋ ህክምና ማእከል በዛሬው እለት በይፋ ተመርቋል ። በዚሁም የምርቃት ስነ-ስርአት ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ…


