ባህላዊና ሃይማኖታዊ እሴቶቻችን የአንድነታችን ማሳያዎች ናቸው – የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ባህላዊና ሃይማኖታዊ እሴቶቻችን የአንድነታችን ማሳያዎች መሆናቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ። አገልግሎቱ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለደመራ እና የመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል። የመስቀል በዓል በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች በደማቅ ከሚከበሩ በዓላት አንዱ ነዉ፡፡ በዓሉ ከባህላዊና ኃይማኖታዊ ክንዋኔነቱ አልፎም ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ ከምትታወቅባቸዉ የማይዳሰሱ ቅርሶች መካከልም አንዱ ነዉ፡፡ የመስቀል በዓል በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም…


