የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ለማስጠበቅ በየጦር ግንባሩ ሽብርተኛዉን የወያኔ ቡድን በመደምሰስ ላይ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ስራዊት አጋርነታችንን ለማስመስከር የሚጠበቅብንን ሁሉ ለመወጣት ዝግጁ ነን ሲሉ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ አመራርና ሰራተኞች ገለጹ።
የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል። መድረኩን የቢሮ ኃላፊና ምክትል የቢሮ ኃላፊ የመሩት ሲሆን “ከሉአላዊነታችን በተጻራሪ የቆመው የህወሃት ሸፍጥ” በሚል ርዕስ መነሻ ጽሁፍ በቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር ሳጅድ አልዪ ቀርቧል። በጽሁፉም ህወሃት በጦር ሜዳው እየገጠመው ያለውን ሽንፈትን ለመሸፈን የለመደበትን የማደናገር ስራ ላይ መጠመዱ ተገልጿል። በዚህም የተሳሳተ ግንዛቤን በመፍጠር ለአለም አቀፍ ማህበረሰቡ…


