የድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ፣ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ በዛሬው እለት በቀበሌ 06 የቤት ቁጥር 2456 የሆነውን የአቶ ወንደሰን ሚሊዮን የፈረሰ መኖሪያ ቤት በአዲስ መልክ ግንባታ የማስጀመሪያ መርሃ- ግብር ተካሄደ፡፡

    በማስጀመሪያ መርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ፣ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀርቢ ቡህ እንደገለፁት በመንግስት በሀገር አቀፍ ደረጃ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ የሚገኘው የቤት ጥገናና እድሳት መርሃ-ግብር በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ አቅመ ደካማ እንዲሁም አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች ተጠቃሚ ለማድረግ በአስተዳደሩ የሚገኙ የመንግስት ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀው በዛሬው እለት የተጀመረው የዚሁ አካል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
    ምክትል ከንቲባው አያይዘውም በቀጣይ ቢሮው እና የቢሮው ተጠሪ ተቋማት የህብረተሰቡን ችግሮችን በመለየት የበጎ አድራጎት ስራዎችን በስፋት እንደሚሰሩ ገልጸው የቤቱ ግንባታ ከ300 ሺህ በላይ በሆነ ወጪ የሚገነባ ሲሆን ቤቱ በአስር ቀናት ውስጥ ተጠናቅቆ ለባለቤቶቹ ርክክብ እንደሚፈፀም ኃላፊው ገልጸዋል፡፡
    ዘገባው የድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ፣ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
    መስከረም 7/2015 ዓ.ም