የሀገር ዋልታና መከታ የሆነውን መከላከያ ሠራዊት እንቀላቀል !

    ሀገራችን ኢትዮጵያ ከውስጥ እና ከውጭ የሚገጥማትን ጠላት በመጠበቅ የሀገረ-መንግሥቱን ህልውና ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና የሚጫወት ወታደራዊ ተቋም በመገንባት ላይ ነች፡፡
    ኢትዮጵያ የገጠማትን ጠላት ቀድሞውንም ወደተመኘው ሲዖል እያወረደች ጎንለጎን ዘመናዊ የመከላከያ ሠራዊት ግንባታ ውስጥ ነች፡፡ ኢትዮጵያን የገጠማት ጦርነት የደመኛ ጠላቶቿ ሰፊ እጅ ያለበት ቢሆንም የማሸነፏ ምስጢር በየደረጃው እየተገነባ ያለው የፀጥታ ኃይል ነው፡፡
    በዚህ ረገድ የሀገር ግንባታው የማዕዘን ድንጋይ በመሆን የአንበሳውን ድርሻ የሚይዘው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ነው፡፡ የሀገር መከላከያ ሠራዊት እንደተቋም ዘላቂ ሰላማችንን፣ ክብርና ነፃነታችን እንዲሁም ኢትዮጵያዊ ማንነታችንን በመጠበቅ ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገታችን እና ለሁንተናዊ የሀገር ብጽግናችን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና ያለው ተቋም ነው፡፡
    የሀገር መከላከያ ሠራዊት ለሕዝብ የቆመ፤ ኢትዮጵያን ያስቀደመ፤ የኢትዮጵያዊያን ውህድ ማንነት ውጤት የሆነ ታላቅ ተቋም ነው፡፡ ወጣቶች ይህን ታላቅ ተቋም በመቀላቀል ለራሳቸው ሰፊ የሥራ ዕድል እንዲያገኙ፤ ለሀገራቸው ደግሞ ታላቅ ታሪክ እንዲሰሩ ሁኔታዎች ተመቻችተውላቸዋል፡፡ የተማሩ ወጣቶች ወደ ተቋሙ በመቀላቀል የፈጠራ ህልማቸውን ሊያሳኩ የሚችሉበት አማራጭ አላቸው፡፡
    መከላከያ እንደተቋም የብዙ ቴክኖሎጅ ተቋማት ባለቤት በመሆኑ ወጣቶች በእነዚህ ተቋማት በመቀላቀል ሀገርን ወደፊት የሚያራምዱ የፈጠራ ሥራዎችን በመፍጠርና በማበልጸግ ለራሳቸው፣ ለሕዝባቸውና ለሀገራቸው የማይሞት ታሪክ መስራት ይችላሉ፡፡