የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ለማስጠበቅ በየጦር ግንባሩ ሽብርተኛዉን የወያኔ ቡድን በመደምሰስ ላይ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ስራዊት አጋርነታችንን ለማስመስከር የሚጠበቅብንን ሁሉ ለመወጣት ዝግጁ ነን ሲሉ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ አመራርና ሰራተኞች ገለጹ።

    የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል።
    መድረኩን የቢሮ ኃላፊና ምክትል የቢሮ ኃላፊ የመሩት ሲሆን “ከሉአላዊነታችን በተጻራሪ የቆመው የህወሃት ሸፍጥ” በሚል ርዕስ መነሻ ጽሁፍ በቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር ሳጅድ አልዪ ቀርቧል።
    በጽሁፉም ህወሃት በጦር ሜዳው እየገጠመው ያለውን ሽንፈትን ለመሸፈን የለመደበትን የማደናገር ስራ ላይ መጠመዱ ተገልጿል። በዚህም የተሳሳተ ግንዛቤን በመፍጠር ለአለም አቀፍ ማህበረሰቡ በማሰራጨት ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠር እየሠራ መሆኑ ተብራርቷል።
    ነዋሪውም በዚሁ የማደናገር ስትራቴጂ ስለባ ሳይሆን ባለው አቅም ሁሉ ማጋለጥ እንደሚገባና በየተሠማራንበት የስራ መስክ ጠንክረን በመስራት እንዲሁም የተጀመረ ው ሁሉ አቀፍ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ተነስቷል።
    የማህበራዊ ሚድያ አጠቃቀማችንን በማሻሻል እንዲሁም አገልግሎት አሰጣጣችንን በማቀላጠፍ የበኩላችንን ማበርከት እንደሚገባ ተጠቁሟል።
    በተጨማሪም የአካባቢያችንን ደህንነት በንቃት ለመጠበቅ መንቀሳቀስ እንደሚገባ ተጠቅሷል።
    ከወቅታዊ ሀገራዊ ውይይቱ በተጨማሪ በመድረኩ ቢሮው በዝግጅት ምእራፍ እእያከናወናቸው የሚገኙ ስራዎች የሁለት ወራት ሪፓርት የቀረበ ሲሆን ቢሮው በበጀት አመቱ ሊያሳካቸው ያስቀመጣቸው ግቦች ለማሳካት በዝግጅት ምእራፍ መከናወኑ የሚገባቸውን ተግባራት በማጠቃቀል ወደ ትግበራ መግባት እንደሚገባ ተገልጿል።
    N.S የመሬት ልማትና ማኔጀመንት ቢሮ ኮሙኒኬሽን ክፍል