🇪🇹 መስከረም 7/2015 የወጣቶች ምክክር መድረክ በድሬዳዋ እየተካሄደ ነው።

    በድሬዳዋ የሚገኙ የከተማ ቀበሌና የገጠር ክላስተር ወጣቶች በወቅታዊ ጉዳዮች ከአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር እየተወያዩ ይገኛሉ፡፡
    ”የአስተዳደራችንን ዘላቂ ሠላም በማረጋገጥ የድሬዳዋ ብልጽግና እውን ለማድረግ የወጣቱ ሚና ከፍተኛ ነው” በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።
    ከወጣቶች ጋር እየተካሄደ በሚገኘው ምክክር መድረክ በሀገራዊ ጉዳይ የጋራ መግባባት ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡