የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ እንዲሁም የአስተዳደሩ የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ በግዳጅ ላይ የቆሰሉና በድሬዳዋ አስተዳደር ኩባ ከንብ የመከላከያ ሆስፒታል ውስጥ ህክሚና ለይ ላሉት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት የንጽህና፣ የአልባሳትና የተለያዩ የቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ።
በድጋፉ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ጫልቱ ሁሴንና ሌሎች የቢሮው አመራሮች ፣ የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ምክትልና የፖለቲካና ርዕዮተ አለም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሻኪር አህመድ ፣ የአስተዳደሩ የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሁክሚያ መሀመድ እና ሌሎችም በመገኘት ከጀግናው ሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን መሆናቸውን በመግለጽ የተጎዱ አባላትን ያበረታቱ ስሆን ድጋፉንም ለካመቡ ሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ አስረክበዋል ።
መ.ም :- የሴቶች፣ህጻናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ


