የስንቅ ማዘጋጀት ስራዉ ላይ የቢሮዉ አመራሮችና መላዉ ሠራተኛ የተሳተፈ ሲሆን የቀድሞ የቢሮዉ ኃላፊ የነበሩና በአሁኑ ሰአት የአሰተዳደሩ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በስንቅ ዝግጅት ፕሮግራሙ ላይ በክብር እንግድነት በመገኘት ሠራተኞችን አበረታተዋል።
በሽብርተኛዉ ቡድን ለ3ኛ ጊዜ በህዝባችን ላይ የተከፈተዉን ጦርነት በቀልበስ የ ሀገራችንን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ህይወቱን ለሰጠን ለጀግናዉ የመከላከያ ሠራዊታችን ጦርነቱ በኢትዮጵያ አሸናፊነት እስኪ ቋጭ ድረስ ህዝቡ ለጀግናዉ የመከላከያ ሠራዊታችን እያደረገ ያለዉን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ገልጸዋል።
በስንቅ ዝግጅት መረሃ ግብሩ ላይ የድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ክቡር አቶ ደረጀ ጸጋዬ እንድሁም የውሃ መዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ክቡር አቶ ኑረዲን አብደላ
የተገኙ ሲሆን የቢሮዉ አመራሮችና ሠራተኞች ከስንቅ ዝግጅት በተጨማሪ ለሠራዊቱ ደም በመለገስ ከሠራዊቱ ጎን መሆናቸዉን አረጋግጠዋል።


