የድሬደዋ አስተዳደርና የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ለቀጣይ 3 ዓመታት በተለያዩ መስኮች ላይ በጋራ አቅደው በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡
የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ከድሬደዋ አስተዳደር ጋር በተለያዩ መስኮች ተቀራርቦ ሲሰራ የቆየ ሲሆን በተለይም ካለፋት ሦስት ዓመት ወዲህ በተለይ በአቅም ግንባታ ፣ በምርምር እና በማኅበረሰብ አገልግሎት የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ አሁን ደግሞ ለቀጣይ ሦስት ዓመት የሚቆይና አስተዳደሩን ድህንትና ስራአጥነትን በመቀነስ ልማትና እድገት ለማረጋገጥ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ የሚያግዙ ስራዎች በተለያየ ማህበራዊ ና ኢኮኖሚያዊ መስኮች ላይ በጋር መስራት እንዲያስችላቸው የጋራ…


