መግብያ
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ጽ/ቤት በአዋጅ ቁጥር 1/2000 ዓ.ም የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነቶች መሰረት አድርጎ ለተገልጋይና ባለድርሻ አካላት በዋናነት ለአስተዳደሩ ምክር ቤትና አባላቱ የህግ አወጣጥ፣ ክትትልና፣ ቁጥጥር እና ውክልና የመወጣት ሙያዊና አስተዳደራዊ አገልግሎቶችን ለመስጠት የ2014 በጀት ዓመት መደበኛ፤የካፒታል እና የፋይናንስ እቅዱን ለምክር ቤቱ ጠቅላላ ጉባኤ አቅርቦ በማጸደቅ በበጀት ዓመቱ የዝግጅትና ትግበራ ምዕራፍ ለዕቅዱ ውጤታማ አፈጻጸም የተንቀሳቀሰ ሲሆን ፡፡
በዚህ መሰረት የአመራር ዑደቱን በተከተለ መልኩ የምክር ቤቱ ጽ/ቤት የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለባለድርሻና ተገልጋይ አካላት ግምገማና ግብዓት አሰጣጥ ግልጽ በሆነ እና በተሟላ መልኩ እንደሚከተለው አቀርባለሁ ፡፡
የዝግጅት ምእራፍ ዋና ዋና ተግባራት አፈጻጸምን በተመለከተ፤
- የዕቅድ ዝግጅትን በተመለከተ የበጀት ዓመቱ የምክር ቤቱ ጽ/ቤት ዕቅድ ከተቋሙ ተልዕኮና በበጀት ዓመቱ ሊሳኩ ከሚገባቸው ስትራቴጃዊ ተግባራት አንጻር ተዘጋጅቶ በምክር ቤቱ እንዲጸድቅ ተደርጓል
- ዕቅድ ኦረንቴሽንን በተመለከተ በበጀት ዓመቱ የተዘጋጀውን የፊዚካልና የፋይናንሻልዕቅድ ሠራተኛ ተወያይቶና ተግባብቶ እንዲተገብረው ለማስቻል የውይይት መድረክ ተዘጋጅቶ ማወያየት ተችሏል፡፡
- በተጨማሪ ለጽ/ቤቱ የህዝብ ክንፍ ዕቅዳችንን አቅርበንና አስገምግመን አስተችተናል፡፡
የፈጻሚውንና የአመራሩንአቅም በስልጠና በመገንባት ረገድ
የለውጥ ስራን የሚተገብር አመራርና ሠራተኛ የበለጠ አቅም ፈጥሮ ወደ ስራ እንዲገባ ከማድረግ አንፃር በ2ኛ ዙር የምክር ቤት አባል ሆነው ሲያገለግሉ ለነበሩና የስራ ዘመናቸውን አጠናቀው በክብር ለተሰናበቱአባላት እና የ3ኛ ዙር ተመራጭ ምክር ቤት አባላት እንዲሁም ለምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች በተለያያዩ ርእሶች ላይ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
በዚሁ መሰረት፡-
- ለ2ተኛው ዙር የምክር ቤት አባላት ስልጠና በመንግስት የስልጣን ክፍፍል፤ በምክር ቤቱ ያለፉት የምርጫ ዘመኖች ዋና ዋና አሰራርና አደረጃጀቶች ዙርያ ስልጠና መስጠት ተችሏል፡
- ለ3ኛ ዙር የምርጫ ዘመን ተመራጭ የምክር ቤት አባላት የመግብያ ስልጠና በሶስት ርእሶች ላይ መስጠት ተችሏል፡፡
- ለምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢና ለጽ/ቤቱ አመራሮች በቋሚ ኮሚቴ ተግባርና ኃላፊነት እንዲሁም በፕሮጄክት ክትትል ዙርያ ስልጠና መስጠት ተችሏል፡፡
- እንዲሁም ለምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አባላት የመግብያ ስልጠና መስጠት ተችሏል፡፡
- ለሴት የምክር ቤት አባላት (ኮኮስ) በፌደራሊዝም ጽንሰ ኃሳብ እና አተገባበር ላይ ስልጠና መስጠት ተችሏል፡፡
- ሠራተኞች በለውጥ መሳሪያዎች ላይ እና ሌሎች የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች ለሰራተኛ በተከታታይ በ Communication skill ፤ Team Builiding ፤ Mind set ፤ work Ethics Plan and reportተሰጥቷል፡፡
የሰው ኃይል በማሟላትና አደረጃጀትንበማጠናከር ረገድ
- በ2013 በጀት ዓመት የተደረገውን የማጠቃለያ ምዕራፍ ግምገማ ውጤት መሰረት በማድረግ ወደ ትግበራ ምዕራፍ ከመገባቱ በፊት በክፍት መደቦች ላይ ሠራተኛን በቅጥር እና በደረጃ ዕድገት አንዲሟሉ ለማድረግ 8 ታቅዶ በአራት ክፍት መደቦች ላይ ቅጥር ማከናወን ተችሏል
- ለቋሚ ኮሚቴ ሙያዊና አስተዳደራዊ አገልግሎት የሚሰጡ ከፍተኛ ሙያተኞች እጥረት ቢኖርም ባሉት ሙያተኞችና በአንድ ኮንትራት ሰራተኛ ጥሩ ሞያዊ ድጋፍ የመስጠት ስራዎች ተሰርቷል፡፡
ግብአትን በማሟላት ረግድም
- ግብዓቶችን በካፒታልና መደበኛ በጀት ለማሟላትና የተጣለውን ግብ ለማሳካት የግዥ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች የስፔስፊኬሽንና የጨረታ ሰነድ በማዘጋጀት አስፈላጊ ግብዓቶች እንዲሟሉና ጥቅም ላይ እንዲውሉ ተደርጓል፡፡
- የምክር ቤቱ ጽ/ቤት ለምክር ቤቱ እና በዋናነት ለምክር ቤቱ አካላት ሙያዊና አስተዳደራዊ ድጋፍና አገልግሎት ለመስጠት የተቋቋመ እንደመሆኑ መጠንም ዋንኛ ተገልጋዮቹ ለሆኑት ለምክር ቤቱ አስተባባሪ እና ለ7ቱ ቋሚ ኮሚቴዎች የራሳቸውን ዕቅድ እንዲዘጋጁ የተሟላ ሙያዊና አስተዳደራዊ አገልግሎት መስጠት፤ የዕቅድ ኦረንቴሽን ለሚመለከታቸው አካላት እንዲሰጡ ማስቻል እና በእያንዳንዱ ቋሚ ኮሚቴ ስር የተደለደሉ የአስተዳደሩ መንግስታዊ ተቋማት ዓመታዊ የመደበኛ፣ የካፒታልና የፋይናንስ ዕቅዶቻቸውን ገምግመው ግብረ-መልስ እንዲሰጡ ማስቻል በዝግጅት ምዕራፍ እንዲከናወኑ የሚጠበቁ መሰረታዊ ስራ በመሆኑ ለእነዚህ ስራዎች ስኬታማነት አስፈላጊ የሆኑ ሙያዊና አስተዳደራዊ አገልግሎቶች ተሰጥቷል፡፡
- ለምክርቤቱ 2ኛውየምርጫዘመንማጠናቀቂያእናየአባላትሽኝትሙያዊናአስተዳደራዊድጋፎችንተደርገዋል
- ለምክርቤቱ 3ኛውየምርጫዘመንየጠቅላላጉባኤውምስረታእናለምክርቤቱውስጣዊአደረጃጀቶችመጠናከርአስፈላጊሙያዊናአስተዳደራዊድጋፎችንተደርገዋል
- የምክርቤቱቋሚኮሚቴዎችበስራቸውየተደለደሉየአስተዳደሩንተቋማትየ2014 በጀትዓመትመደበኛእናየካፒታልእቅዶቻቸውንገምግመውግብረ-መልስእንዲሰጡየሚስችሉሙያዊእናአስተዳደራዊአገልግሎቶችንከመስጠትረገድየምክርቤቱንቋሚኮሚቴዎችበወቅቱያልተሟሉየነበሩቢሆንምይህንክፍተትታሳቢያደረገፕሮግራምእናአሰራርበመዘርጋትዕቅዱሙሉለሙሉተፈጻሚተደርጓል
በተጨማሪም እንደ አስተዳደርበተቀመጠው አቅጣጫና የጊዜ ገደብ ውስጥ ጥራት ያለው እና የተሟላ ይዘት ያለው የ60 ቀን ፈጣን ምላሽ አምጭ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ፤በአስተባባሪ ኮሚቴና (ነባር ቋሚ ኮሚቴ አመራሮች ጭምር በተገኙበት) በምክር ቤቱ ጽ/ቤት ማኔጅመንት አባላት እንዲገመገም፤እንዲዳብር፤እንዲጸድቅ እና ለሚመለከታቸው አካላት አንዲሰራጭ በማድረግእና በዕቅዱ ተይዘው የነበሩና ጽ/ቤቱን የሚመለከቱ ተግባራት በጥሩ ሁኔታ ተፈጻሚ እንዲሆኑ የሚስችሉ አበረታች ስራዎች ተሰርተዋል
የትግበራ ምዕራፍ አፈፃፀም
ህግ ማውጣትን በሚመለከት
በበጀት ዓመቱ በጽ/ቤቱ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ መሰረት10 ረቂቅ ህጎችን ተቀብሎ በቋሚ ኮሚቴና በደጋፊ ባለሞያዎች እንዲታዩ እና ለጠቅላላ ጉባኤው ቀርበው እንዲፀድቁ፣ለማድረግ በታቀደው መሰረት እንደሚከተለው ተከናውናል፡፡
- የ2013 ተጨማሪ በጀት አዋጅ ቁጥር 65/2013፤ የመሬት ይዞታ አስተዳደር ጽ/ቤትን ለማቋቋም እና ተግባርና ኃላፊነቱን ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁጥር 66/2013እና የ2013 በጀትአዋጅ ቁጥር 67/2013በድሬ ነጋሪት ጋዜጣታትመው ለሚመለከታቸውአካላት እንዲሰራጩ እየተደረገ ሲሆን በሶስት አዋጆች ላይ ማለትም በድሬደዋ አስተዳደር አስፈጻሚ አካላትን አንደገና ለማደረጀት የጸደቀውን አዋጅ ቁጥር 68/2014፤የከተማ መዋቅራዊ ፕላን ኢንስቲቲዩት ማቋቋሚ አዋጅ 69/2014እና የድሬደዋ አስተዳደር ከተማ መዋቅራዊ ፕላን አዋጅ ቁጥር 70/2014 ቴክኒካል እርምት በማድረግ ወደህትመት ለመላክ በሂደት ላይ ይገኛሉ፡፡
- የምክር ቤቱ ጽ/ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ስራው በቴክኒክ ኮሚቴ ደረጃ እንዲጠናቀቅ ተደርጓል
- የምክር ቤቱ ቁጥር የአባላት ስነ ምግባር ደንብ ቁጥር 11/2009 የማሻሻል ስራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ
- ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የአስተዳደሩን ቻርተር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ሰነድ እንዲዳብርናለሚመለከታቸው አካላት እንዲቀርብ ሙያዊና አስተዳደራዊ ድጋፍ መስጠት ተችሏል፡፡
- ሶስት ደንቦች የንግድስራዎችን ስርዓት ለማስያዝ የወጣ ደንብ ቁጥር 25/2014፤ድሬደዋ ደወሌ ምድር ባቡር ድርጅትን ለማቋቋም የወጣ ደንብ ቁጥር 26/2014 እና አከራዮች በተከራዮች ላይ የኪራይ ዋጋ እንዳይጨምሩና ከቤት ማስወጣት የሚከለክል (ለአምስት ወር የሚከለክል) ደንብ ቁጥር 27/2014 ከሌሎች ህጎች ጋር የተጣጣሙ መሆናቸውን የማረጋገጥ ተግባር በማከናወን ምዝገባ ተደርጓል፡፡
- አንድ የፋይናንስ ማሻሻያ ረቂቅ ህግ ላይ አስረጂዎች ቀርበው እንዲያስረዱና የመጀመሪያ ደረጃ ንባብ ለማድረግ የሚስችሉ ሙያዊና አስተዳደራዊ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡
- የምክርቤቱ የሴቶች ኮከስ መመሪያ ከደንቡ ጋር የተጣጣመ መሆኑን የማረጋገጥ ስራዎች ተሰርተዋል ፡፡
ክትትልና ቁጥጥር በሚመለከት
የክትትልና ቁጥጥር ሙያዊና አስተዳደራዊ ድጋፎችን በተመለከተም በየሩብ ዓመቱ በየቋሚ ኮሚቴዎቹ ለሚካሄዱ የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች ሙያዊና አስተዳደራዊ አገልግሎቶችን በመስጠት ረገድ ፡፡
- በ2ኛው ዙር የመስክ ምልከታ በምክር ቤቱና በምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች የተሰጡ ግብረ-መልሶች፤ በምክር ቤቱ አባላት የህዝብ ውክልና አወጣጥ መድረክ ህብረተሰቡ ያነሳቸውን የልማትናየመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች፤ የተቋማት አጠቃላይ የመደበኛ ተግባራት የ9ወራት እቅድ አፈጻጸም፤ሴክተር ዘለል ጉዳዮችእናየተቋማት የካፒታል እቅዶች እና የፕሮጀክቶችአተገባበር አፈፃፀም፤በተሰጠው የትኩረት አቅጣጫ በተደረገው የመሰክ ምልከታ እና ሪፖርት አፈፃጸም ግምገማ የተገኙትን ግኝቶችን በጽ/ቤት ደረጃ እንዲሁም በአስተባበሪ ኮሚቴ እንዲገመገም አስፈላጊ ሙያዊ አገልግሎቶች ተሰጥተዋል ፤የመሰክ ምልከታ ሪፖርት ሰነድለ7ቱም ቋሚ ኮሚቴ ለሚከታተሏቸው ተቋማት የጽሁፍ ግብረ መልሶች ተዘጋጀተው እንዲላኩ ተደርገዋልየአስፈፃሚ ተቋማትን የ2014 በጀት ዓመት ማጠቃለያ ምዕራፍ ዕቅድ አፈፀፀም ሪፖርት ፤ የ5 እና የ10 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ እንዲያስገቡ የተከናወኑ የመረጃ ስራዎች ተከናውነዋል፤
- ከተወካዮች ምክርቤት የውሃ፤ መስኖ ፤ቆላማ አካባቢ እና አካባቢ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአስተዳደራችን በተደረገው መስክ ምልከታ በግምገማ መድረክ ሙያዊ ድጋፍ መደረጉ፤
- በመንግስት ወጪ አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ በተዘጋጀው ሄሪንግ መድረክ በፋይናንሻል ህጋዊነት 45 ተቋማትን እና በክዋኔ ኦዲት የ3ተቋማት የ2013 በጀት ዓመት የሂሳብ ኦዲት ሰነዶች ላይ በተደረጉ ምርመራሙያዊ ድጋፍ ተደርጓል ፤
- የአስተዳደሩ ነዋሪዎች ለምክር ቤቱ የሚያቀርቧቸውን ቅሬታና አቤቱታዎች ከማስተናገድ ረገድ ሁለት ከመሬት ይዞታ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ቅሬታዎች ታይተዋል
ውክልና አወጣጥን በተመለከተ
- የምክር ቤቱ ሌላው ተግባር የውክልና መወጣት ሲሆን በዚህም ከህዝብ ጋር በልማት በመልካም አስተዳደርና በሌሎችም አስተዳደራዊም ሆነ ሀገራዊ አጀንዳዎች ዙሪያ ከፌዴራል ተወካዮች ምክር ቤትና ከክልሎች ምክር ቤት በጋራ በመሆን በህዝብ መድረክ የተነሱ ጉዳዮች ተቋማት ምላሽ እንዲሰጡ ግብረ-መልስ ተሰቷል፡፡
በልምድ ልውውጥየምክር ቤቱ አመራርና ቋሚ ኮሚቴዎች አቅምና ግንዛቤ ከማሳደግ ረገድ፡-በሲዳማና በደቡብ ብሔርብሔረሰቦች ክልላዊ መንግስት በተደረገው የልምድ ልውውጥ ተሞክሮ መቅሰምያ የሚውሉ ሁለት ቼክ ሊስቶች ተዘጋጅተውእንዲላኩበማድረግ በሁለቱ ክልሎች በመገኘት ተሞክሮዎችን በማሰባሰብ አንድ ተሞክሮ ሰነድ ማዘጋጀት ተችሏል
የተዋረድ ምክር ቤቶችን በተመለከተ
- የተዋረድ ምክር ቤቶችን ሙያዊ ድጋፍና ስልጠናእንዲያገኙ ተደርጓል
- የተዋረድ ምክር ቤቶች በየቀበሌዎቻቸው ያሉ የህፃናት ፓርላማ አባላትን የማጥራትና የማደራጀት ስራዎች ተሰርተዋል
- የተዋረድ ምክር ቤቶች ከምክር ቤቱ ጽ/ቤት ሞያተኞች ጋር የአቅም ግንባታ ስልጠና ማግኘት ተችሏል፡፡
ቅንጅታዊ ስራዎችን በተመለከተ
- ምክር ቤቱና ጽ/ቤቱ ከፌዴራልና ከአስተደደሩ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ረገድ በወጡ ህጎች አተገባበርና አመዘጋገብ ዙርያ የጥናት ስራውን ከፍትህ ቢሮ፤ከካቢኔ ጉዳዮች ጽ/ቤት ጋር ቅንጅታዊ ስራዎች ተጀምረው በሂደት ላይ ይገኛሉ፡፡
- በሌላ በኩል የአስተዳደሩን ቻርተር የማሻሻል ቅንጅታዊ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡
የጥናትና ምርምር ስራዎች በተመለከተ
በምክር ቤቱ 2ኛ የምርጫ ዘመን ማጠናቀቅያ ላይ ተዳክመውከነበሩናበቀጣይመጠናከር ከሚገባቸው 5 ምክር ቤታዊ የአሰራርና የአደረጃጀት ጉዳዮች ላይ ማለትም በም/ቤቱ ጽ/ቤት አደረጃጀትና አሰራር ዙርያ፤ በምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት ስነ-ምግባር ደንብ፤በምክር ቤቱ የህግ ማውጣት ሂደት ፤ በምክር ቤቱ የክትትልና ቁጥጥር አሰራር እና በም/ቤቱ ጽ/ቤት የህዝብ ተሳትፎ እና በመሳሰሉት የዳሰሳ ጥናት ስራዎች ሙሉለሙሉ ተሰርተዋል፡
የጉባኤ ስራዎችን በሚመለከት
ምክር ቤቱ የሚያከናውናቸውን ተግባራት ለማስተዋወቅና ለማሳወቅ እንዲሁም የምክር ቤቱን ገጽታ ለመገንባት የተገልጋይና ባለድርሻ አካላትን ግንዛቤ ማሳደግ አንዱ የምክር ቤቱ ጽ/ቤት ስትራቴጂክ ግብ በመሆኑ ምክር ቤቱ የሚያካሂዳቸው ተግባራት ህብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲኖረው በጽሁፍ፣ በሬዲዮ፣ በቴሌቪዥንና በተለያዩ መረጃ መስጫ መንገዶች ለማሳወቅ የተለያዩ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ በመሆኑም በበጀት ዓመቱ ውስጥ ምክር ቤቱ ያከናወናቸው ስራዎችን የሚገልጹ 5ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ታቅዶ የቋሚ ኮሚቴ መስክ ምልከታ መደበኛ ጉባኤዎች እንዲሁም የህፃናት ፓርላማን በተመለከተ 4 ጋዜጣዊ መግለጫ ማስተላለፍ ተችሏል፡፡
የምክር ቤት አባላትን አስተያየት ማሰባሰብና የአገልግሎት በማሻሻል የምክር ቤት አባላትን ውጤታማነት ከማሳደግ አንፃር የፕሮቶኮል ፣ የዶክመንት ዝግጅትና ስርጭት እና የጉባኤ ጥሪ አገልግሎቶችን በተቀናጀ ሁኔታ በመስጠት የምክር ቤት አባላትን እርካታ ማሳደግ ተችሏል፣
በአመት 4 ጊዜ በቋሚ ኮሚቴዎች የክትትልና ቁጥጥር ተግባራትግኝቶችን ለህብረተሰቡ በማድረስ የተጠያቂነት አሰራርን ማጎልበት አንፃር ሁለት ድንገተኛ ጉብኝትሁለት መደበኛየመስክ ምልከታ ጉብኝትእና የቋሚ ኮሚቴ አባላት ክትትል ቁጥጥር ስራዎች ለህብረተሰቡ ማድረስ ተችሏል፡፡
- በምክር ቤቱ የተከናወኑ ተግባራትን የሚያሳዩ 1 የአዳራሽ አውደ-ርዕዮች ለማዘጋጀት ታቀደው በታቀደው መሰረት 1 በ3ኛ ዙር 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ተዘጋጅተው መቅረብ ተችሏል፡፡
- በአመቱ በሚከበሩ 8 ብሔራዊ በዓላት በምክር ቤቱ ስም የመልካም ምኞት መግለጫ ለማስተላለፍ አቅዶ ሁሉንም በማስተላለፍ ስራላይ ማዋል ተችሏል፡፡
- የምክር ቤቱንእንቅስቃሴ መረጃ የሚጡ ወቅታዊ ዜናዎች በማህበራዊ ሚድያዎች/face book/ ለማሰራጨት ታቅዶ የምክር ቤቱ መደበኛ ጉባኤዎችና አስቸኳይ ጉባኤ እንዲሁም የቋሚ ኮሚቴ መስክ ምልከታ በቴሌግራም በ3ቱ ቻናሎች ላይ ተጭነዋል በዚሁ መሰረት፡-
- በ189 ምክር ቤት አባላት ቻናል
- የቋሚኮሚቴ አባላት ቻናል
- የቀበሌ ምክር ቤት አፈጉባኤዎች ቻናል ላይ ማሰራጨት ተችሏል፡፡
- የምክር ቤቱን አሰራርና የሥራ እንቅስቃሴ አስመልክቶ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማዳበር የሚያስችል ጥያቄና መልስ ውድድር በጥቅሉ 144 ጊዜ ለማስተላለፍ ታቅዶ በታቀደው መሰረት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ ተችሏል፡
- ከዚህ በተጨማሪ በ2014 በጀት ዓመት የተካሄዱመደበኛ ጉባኤ እና 7ኛአስቸኳ ጉባኤዎች ቃለ-ጉባኤ በማዘጋጀት ሙሉ በሙሉ በተያዘለት ጊዜ ተጠናቆ ለአባላት እንዲደርስ ማድረግ ተችሏል፡፡
- ቀልጣፋና ጥራት ያለው የጉባኤ አገለግሎት በመስጠት የምክርቤት አባላትን እርካታ ማሳደግን አስመልክቶ መደበኛ ጉባኤዎች እና 7ኛ አስቸኳይ ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ ማካሄድ ተችላል፡፡
ብሄራዊ መግባባትን የሚፈጥሩ ተግባራት
በዘንድሮዓመት በ2014 ጥቅምት በገባ በ1ኛ ሳምንት የመጀመርያውሰኞ ዕለትየሚከበረውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን በተመለከተ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተቀመጠው መሪ ቃል መሰረት በማድረግ በምክር ቤቱ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ዉስጥ የምክር ቤቱና የብዙሃን መገናኛ ሰራተኞች በተገኙበት በተከበሩት የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ አማካኝነት በሰንደ ቀላማ መስቀል ሥነ-ስርዓት በደመቀ ሁኔታ አክብሮ መዋል ተችሏል፣
የ16ኛው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በሚመለከት የተቀመጠውን መሪ ቃል መሰረት በማድረግ መነሻ እቅድና የትግበራ እቅድ ተበማዘጋጀት፤ ቴክኒካል ኮሚቴ በማቋቋም፤ንዑስ ኮሚቴ በሁሉም የከተማና የገጠር ቀበሌዎች በማቋቋም በተለያየ ዝግጅት እንዲከበር ከየቀበሌ ምክር ቤት አፈጉባኤዎች እና ከመስተዳደሩ አመራሮች ጋር በተቀናጀ መልኩ በተሰራው ስራ የፓናል ውይይቶች፣ የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድሮች፤ በማድረግ በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ መዋል ተችሏል፡፡
ሴክተር ዘለል ጉዳዮች ማህበራዊ አገልግሎቶችን በተመለከተ
- በስርዓተፆታና በኤች.አይ.ቪ ኤድስ ሚኒስትሪሚንግና ነጭ ሪቫን ቀን ላይ በጽ/ቤቱ ለሚገኙ 47 ሠራተኞች ግንዛቤ ለማስጨበጥ በታቀደው መሰረት 48 ሠራተኛውን የአለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ ከምክር ቤቱ ጽ/ቤት ለተውጣጡ 48 ሠራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት የተካሄደ ሲሆን በስርዓተ ፆታ ላይ ለ21 ወንድና ለ23 ሴት ሠራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ታቅዶ ለ21 ወንድና ለ23 ሴት ሠራተኞች መስጠት ተችሏል፣
- በኤች.አይ.ቪ ኤድስ ምክንያት ወላጆቻቸውን ላጡ ሁለት ህፃናት አመቱን ሙሉ ሰባት ሰባት መቶ ብር ድጋፍ የተደረገ ሲሆን ለ23 ተማሪዎች ለአመት ትመህርት የሚበቃ የትምህርት ቁሳቁስና ዩኒፎርም በ80,000.00 ብር በሚገመት እንዲሟላ በማድረግ ማከፋፈል ተችሏል፣፡
በጀት አጠቃቀምን በሚመለከት
- የምክር ቤቱ ጽ/ቤት በበጀት ዓመቱ ሊያከናውናቸው ካቀዳቸው ስትራቴጂያዊ ግቦችና ዒላማዎች አንፃር ከላይ የተጠቀሱትን የምክርቤቱ ጽ/ቤት አበይት ተግባራትና ሌሎች ተጨማሪ ስራዎችን ጨምሮ የ2014 በጀት ዓመት የፊዚካል እቅድ አፈፃፀም በአጥጋቢ ሁኔታ ማከናወን የተቻለ ሲሆን በበጀት ዓመቱ ለመደበኛ ስራ ማስኬጃ ብር 25.841.317.00 ብር/ ተመድቦ ከዚህ ውስጥ የተመደበው በጀት ሙሉ በሙሉመቶ ፐርሰንት ስራ ላይ የዋለ ሲሆን የካፒታል በጀት ብር15.100.000.00ብር/ ተመድቦ ለታቀደለት ስራ መዋል ተችሏል፡፡
የ2014 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ማጠቃለያ ግምገማ
- የአመራር ዑደቱን በተከተለ የእቅድ አፈጻጸም ሂደት በየምዕራፉ ሊከናወኑ ከሚገባቸው ዋና ዋና የክትትልና ግምገማ አይነቶች መካከል አንዱና ዋንኛው የእቅዱን ዋና ዋና ውጤታማ አፈጻጸሞች እና በእቅድ ዘመኑ የነበሩ ዋና ዋና የአፈጻጸም ውስንነቶች እና ማነቆዎች በእቅድ ዓመቱ ማጠቃለያ ምእራፍ ላይ በሚገባ ተገምግመው ለቀጣዩ በጀት ዓመት አቅድ ዝግጅት እናቀጣይነት ያለው ውጤታማነት እንዲረጋገጥ የግምገማ ውጤቶች ግብአት የሚደረጉበት አግባብ ነው ፡፡
በዚህ መሰረት የም/ክርቤቱ ጽ/ቤት በበጀት ዓመቱ አቅዶ በሚገባ ከፈጸማቸው ዋና ዋና ግቦች ፤በበጀት አመቱ ካከናወናቸው ውጤታማ ስራዎች ፤ በበጀት አመት አቅድ አፈጻጸሙ ከነበሩበት ውስንነቶች እና ካጋጠሙት ተግዳሮቶች አንጻር የ2014 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸሙን በማጠቃለያ ምእራፍ አንደሚከተለው ገምግሞ የአፈጻጸም ሪፖርቱ አካል አድርጎ አቅርቧል፡፡
- የህግ አወጣጥ ክትትልና ቁጥጥር ሙያዊ ድጋፍ አሰጣጥ ጽ/ቤቱ የ2013 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ መሰረት በማድረግ እና በ2014 በጀት ዓመት መከናወን የሚገባቸውን ጽ/ቤቱ ስትራቴጃዊ ተግባራት መሰረት በማድረግ የ2014 በጀት ዓመት እቅዱን አቅዶ እና በሚመለከታቸው አካላት አጸድቆ ወደስራ መግባቱ እና እቅዱንም የአመራር ኡደቱን በተከተለ መልኩ ከዝግጅት ምእራፍ አስከ ማጠቃለያ ምእራፍ ሲከናውን የቆየ መሆኑ ይታወቃል ፡፡
- በዚህ መሰረት የምክርቤቱ ጽ/ቤት አጠቃላይ የበጀት ዓመቱ የእቅድ አፈጻጸም እና ውጤታማነት ሲታይ ጽ/ቤቱ ከተቋቋመለት ዓላማ አንጻር እና በ2014 በጀት ዓመት ሊከናውናቸው ከሚገቡ ምክር ቤታዊ ሙያዊና አስተዳደራዊ ተግባራቶች በብዙ መልኩ ውጤታማ ስራዎች መስራት የተቻለበት ለአስተዳደሩ ልማትና መልካም አስተዳደር ግንባታም ሆነ ለምክር ቤቱ ተልእኮ ስኬት ጽ/ቤቱ ከፍተኛ አዎንታዊ ሚና ሊያበረክቱ የሚችሉ ስራዎችን የሰራበት ዓመት ነበር ማለት ይቻላል፡፡ከዚህ አኳያ በበጀት ዓመቱ በግብ የተያዙ የጽ/ቤቱ ዓመታዊ አቅዶች ዋና ዋና ተግባራት በሚገባ ከመፈጸም ረገድ በአማካይ 96% በላይ የእቅድ አፈጻጸም በማስመዝገብ የበጀት ዓመቱን ያጠናቀቀ መሆኑ አበረታች ነው ፡፡
ከእቅድ ውጪ የተሰሩ ስራዎች
የደሬደዋ አስተደደር ምክር ቤት በ3ኛው ምርጫ በ1ኛ ስራዘመን ከዚህ በፊት ለረጅም ዘመን እድሳት ሳያገኙ አገልግሎት በመስጠት ላይ የነበሩ የአፈጉባኤ ቢሮ፤ የምክትል አፈጉባኤ ቢሮ፤ የቋሚ ኮሚቴዎች ቢሮ፤ የትንሻ አደራሽ እና ላይብረሪ እድሳት እጅግ ዘመናዊ በሆነ መልኩ ለሌሎች ተቋማትም ምሳሌ መሆን በሚችል ወጪቆጣቢ በሆነ መልኩ ማደስ የተቻለ ሲሆን ቀሪ ቢሮች በ2ኛ ስራ ዘመን ውስጥ የሚታደሱ ይሆናሉ፡፡
አመሰግናለሁ!!!
ድሬደዋ


