November 23, 2022
የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት የ2014 በጀት ዓመት ፊዚካል ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት
መግብያ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ጽ/ቤት በአዋጅ ቁጥር 1/2000 ዓ.ም የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነቶች መሰረት አድርጎ ለተገልጋይና ባለድርሻ አካላት በዋናነት ለአስተዳደሩ ምክር ቤትና አባላቱ የህግ አወጣጥ፣ ክትትልና፣ ቁጥጥር እና ውክልና የመወጣት ሙያዊና አስተዳደራዊ አገልግሎቶችን ለመስጠት የ2014 በጀት ዓመት መደበኛ፤የካፒታል እና የፋይናንስ እቅዱን ለምክር ቤቱ ጠቅላላ ጉባኤ አቅርቦ በማጸደቅ በበጀት ዓመቱ የዝግጅትና ትግበራ ምዕራፍ ለዕቅዱ ውጤታማ አፈጻጸም…
የምክር ቤቱ ተልዕኮ
የምክር ቤቱ አባላትና አካላት የህግ አወጣጥ ክትትልና ቁጥጥር እንዲሁም የውክልና ስራ በመተግበር እንዲያከናወኑ ሙያዊ ድጋፍና አስተዳደራዊ አገልግሎት በተሟላ መልኩ መስጠት፡፡
በድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ እና የቢሮው ተጠሪ ተቋም በሆነው የድሬዳዋ ሥራ አመራር እና ካይዘን ኢንስቲትዩት አመራሮች እና ሠራተኞች ከራስ ለራስ የተደረገ የበጎ ተግባር ውጤት::
የድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ እና የቢሮው ተጠሪ ተቋም የሆነው የድሬዳዋ ሥራ አመራር እና ካይዘን ኢንስቲትዩት አመራሮች እና ሠራተኞች በ 01ቀበሌ ሲያስገነቡት የነበረውን የወ/ሮ አሁዶ ጅብሪል አጠናቀው በዛሬው እለት አስረክበዋል:: በአስተዳደር ደረጃ በየአመቱ በሚከናወነው የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎቶች ሁሉም የአስተዳደሩ የመንግስት ተቋማት እዲሳተፉ አቅጣጫ መቀመጡን ተከትሎ በዘንድሮው ክረምት የድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ…
የስራ ክህሎት እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ እና ተጠሪ ተቋማት የ17ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች በዓል ምክኒያት በማድረግ በዛሬው እለት ህብረብሄራዊ አንድነት ለዘላቂ ሰላማችን በሚል መሪ ቃል በኢትዩ ጣሊያን መሰብሰቢ አዳራሽ ውይይት ተደርጓል፡፡
የውይይት መድረኩ በንግግር የከፈቱት የቴክኒክ እና ሞያ ቢሮ የልህቀት ማዕከል ሀላፊ አቶ ካሊድ መሀመድ ሲሆን የመወያያ ሰነድ ቀርቦ ሀሳብ አስተያየት ተሰጥቶበት ውይይት ተደርጓል፡፡ በኢትዮ ጣሊያን ኮጅ አሰልጣኝ መምህርት ሄለን ደረጀ በሰጡት አስተያየት የብሄር ብሄረሰቦች በዓል በሀገራችን በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች ከአለባበሳችን ጀምሮ አኗኗራችን እና ቋንቋችን የተለያየ አንድነት ወበት ያለን መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይህ እንዲህ እንዳለ የአንዱን ብሄር…
የኢትዮጲያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በአል በተለያዩ የከተማዋ ቀበሌዎች ላይ ተከበረ።
ሀገራችን ኢትዮጲያ የበርካታ ቋንቋ ፣ ባህል እሴት ባለቤት ከመሆኗም በዘለለ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች በመከባበር ፣ በመተሳሰብ ብሎም በመቻቻልና በአንድነት በመሆን የሚኖሩባትም ሀገር ነች ። ይህንንም የሀገራችን ልዩ መገለጫ የሆነውን የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ላለፍት አመታት በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች ሲከበር ቆይቷል ። በያዝነው አመትም ለ 17 ተኛ ጊዜ የሚከበረው የኢትዮጲያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በአል በሲዳማ…
- 1
- 2


