የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት በድሬዳዋ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 416/1996 የተቋቋመ የአስተዳደሩ ሥልጣን መገለጫ ተቋም ነው፡፡ ምክር ቤቱ የመጀመሪያውን የስራ ዘመኑን ሰኔ 5 ቀን 2000 ዓ.ም በህዝብ በተመረጡ 189 የምክር ቤት አባላት የተመሰረተ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ሶስተኛውን የስራ ዘመን ከመስከረም 19 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የተለያዩ ለምክር ቤቱ የተሰጡትን ተግባርና ኃላፊነት በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ምክር ቤቱ ለመልካም አስተዳደር መስፈን ለሰብአዊ መብቶች መከበር ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታና ለዘላቂ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማትን ለማረጋገጥ የሚውሉ ህጎችን በተጠናከረ የህዝብ ተሳትፎ በማውጣትና ተግባራዊነታቸውን በመከታተልና በመቆጣጠር የአስተዳደሩ ህብረተሰብ ኑሮ ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲያድግ በሚደረገው እንቅስቃሴ የጎላ አስተዋጽኦ በማድረግ ሃላፊነቱን በመወጣት ላይ የሚገኝ አካል ነው፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት በህዝብ የተጣለበትን አደራና ህገ-መንግስታዊ ሃላፊነቱን በመወጣት ለተገልጋይና ለባለድርሻ አካላት ስለተቋሙ ልዩ ልዩ መረጃዎች ለመስጠት ይህ ፖርታል ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡


