የስራ ክህሎት እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ እና ተጠሪ ተቋማት የ17ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች በዓል ምክኒያት በማድረግ በዛሬው እለት ህብረብሄራዊ አንድነት ለዘላቂ ሰላማችን በሚል መሪ ቃል በኢትዩ ጣሊያን መሰብሰቢ አዳራሽ ውይይት ተደርጓል፡፡

    የውይይት መድረኩ በንግግር የከፈቱት የቴክኒክ እና ሞያ ቢሮ የልህቀት ማዕከል ሀላፊ አቶ ካሊድ መሀመድ ሲሆን የመወያያ ሰነድ ቀርቦ ሀሳብ አስተያየት ተሰጥቶበት ውይይት ተደርጓል፡፡
    በኢትዮ ጣሊያን ኮጅ አሰልጣኝ መምህርት ሄለን ደረጀ በሰጡት አስተያየት የብሄር ብሄረሰቦች በዓል በሀገራችን በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች ከአለባበሳችን ጀምሮ አኗኗራችን እና ቋንቋችን የተለያየ አንድነት ወበት ያለን መሆኑን ገልጸዋል፡፡
    ይህ እንዲህ እንዳለ የአንዱን ብሄር ለሌላው ብሄር ማወቅም ጥቅም እንዳለው ጠቅሰዋል፡፡ አያይዘውም በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍልም የሚኖሩ ብሄሮችን አለባበሳቸውን አኗኗራችውን እንዲሁም ቋንቋችውን ማውጣት እንዳለብን ይህም ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለቱሪስትም መስህብ ወበትም እንደሆነ መምህርት ሄለን ገልጸዋል፡፡
    በአሁኑ ሰዓት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ብዙ ጦርነት ነበር አሁን ላይ ግን ሰላም መምጣቱን ጠቅሰው አሁን የመጣውን ሰላም በማስቀጠል ብሄርን ሽፋን አድርጎ የሚሰሩ ስራዎች በመጸየፍ አንድነታችንን አጎልተው በማውጣት ተከባብረው መኖር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡