የኢትዮጲያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በአል በተለያዩ የከተማዋ ቀበሌዎች ላይ ተከበረ።

    ሀገራችን ኢትዮጲያ የበርካታ ቋንቋ ፣ ባህል እሴት ባለቤት ከመሆኗም በዘለለ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች በመከባበር ፣ በመተሳሰብ ብሎም በመቻቻልና በአንድነት በመሆን የሚኖሩባትም ሀገር ነች ። ይህንንም የሀገራችን ልዩ መገለጫ የሆነውን የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ላለፍት አመታት በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች ሲከበር ቆይቷል ። በያዝነው አመትም ለ 17 ተኛ ጊዜ የሚከበረው የኢትዮጲያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በአል በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስተናጋጅነት በታላቅ ድምቀት ይከበራል ።

    በድሬዳዋ አስተዳደር ላይም ከህዳር 7 ቀን 2015 ዓ.ም አንስቶ የኢትዮጲያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በአል በሁሉም የከተማ ቀበሌዎችና የገጠር ክላስተሮች ላይ በተለያዩ መርሀ-ግብሮች የሚከበር ሲሆን በዛሬው እለትም በ 03 ፣ 04 ፣ 05 ቀበሌዎች ላይ እንዲሁም በድሬዳዋ ደወሌ ምድር ባቡር ቅጥር ጊቢ ውስጥ በፓናል ውይይት ተከብሯል ። በዛሬው እለትም በተለያዩ የከማዋ ቀበሌዎች እንዲሁም ደግሞ በድሬዳዋ ደወሌ ምድር ባቡር 17 ተኛው የኢትዮጲያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በአል ህብረ-ብሔራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን በሚል መሪ ቃል በፓናል ውይይት ሲከበርም የከተማዋ ነዋሪዎች ተሳታፊ በመሆን ሰፊ ውይይት አድርገዋል ።