በድሬዳዋ አስተዳደር ላይ እየተገነቡ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶችን ከፍተኛ የአስተዳደሩ አመራሮች ጎበኙ

በድሬዳዋ አስተዳደር ላይ እየተገነቡ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶችን ከፍተኛ የአስተዳደሩ አመራሮች ጎበኙ።

በድሬዳዋ አስተዳደር በ 2015 በጀት አመት በፌደራል መንግስት ከሚሰሩት የልማት ፕሮጀክቶች ውጪ ከ 170 በላይ የሚሆኑ የልማት ፕሮጀክቶች ለመስራት የታቀዱ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 5 ግዙፍ የልማት ፕሮክቶችን በመምረጥ እነዚህም የልማት ፕሮጀክቶች ያሉበትን ሁኔታ ከመገምገም ባለፈ ከፕሮጀክቶቹ ጋር ተያይዞ ያሉትን የካሳ ክፍያ ጥያቄዎች በተጨባጭ ለማየትና ለመገምገም ይቻል ዘንድ በዛሬው እለት ከፍተኛ የአስተዳደሩ አመራሮች ጎብኝተውታል ።

በዛሬው እለትም ጉብኝት የተደረገባቸው የልማት ፕሮጀክቶች ከድሮ ኬላ እስከ አዲሱ የጅቡቲ መንገድ ድረስ ያለው 4 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር መንገድ ፣ ከመልካ ጀብዱ አንስቶ እስከ ነፃ የንግድ ቀጠና ድረስ የሚደርሰው መንገድ ፣ ከሰባተኛ እስከ መሬት ልማት ( ቦረን ) ያለው መንገድና ተለዋጭ እየተሰራ ያለውን ድልድይ ፣ ገንድ ተስፋ አካባቢ ያለው መንገድ እንዲሁም መምሪያ አካባቢ የሚገኘው ሲዮስታ ሆቴልን የሚያቋርጠውን መንገድ ጎብኝተውታል ።

በተለይም በልማት ፕሮክቶቹ አማካኝነት የሚነሱ የህብረተሰብ ክፍሎችን ሌላ አካባቢዎች ላይ የሚሰፍሩባቸውን መንገድ ለማየትና የሚሰሩ ፕሮጀክቶችንም በተጨባጭ ቦታው ድረስ በመመልከትና የአስተዳደሩ ካቢኔም በጉዳዩ ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠትና በመወያየት በፕሮጀክቶቹ ዙሪያ ውሳኔ እንደሚሰጥም ነው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ሀርቢ ቡህ የተናገሩት ።