ለሠላም ስለሠላም የተከፈለውን ዋጋ ልናከብረው ይገባል
ለሁላችንም መተኪያ የሌላት እና የጋራ መኖሪያችን የሆነችውን ሀገር የመገንባቱ ኃላፊነት የሁላችንም ነው፡፡ ሀገርን የመገንባት አጀንዳዎቻችን ላይ የጋራ መግባባትን ለመፍጠር ተጨማሪ ጊዜ ልናባክን አይገባም፡፡ ይህችን ሀገር ለመገንባት ትውልድ ሁሉ በየተራው ይሄ ነው ተብሎ እንዲህ በቀላሉ በአንደበት ሊገለጽ የማይቻል ትልቅ ዋጋ ከፍሏል፡፡ ይህን ለሠላም ስለሠላም የተከፈለ ክቡር ዋጋ ማክብር እና ጠብቆ ማቆየት የአሁኑ ትውልድ የሞራል ግዴታ ነው፡፡…


